በ2014 ዓ.ም በከፍተኛ ሊግ የምድቡ የበላይ ሆኖ በመጨረስ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያደገዉ የለገ ጣፎ ለገዳዲ እግር ኳስ ክለብ ከፍተኛ የበጀት እጥረት እንዳጋጠመዉ እና በተጨዋቾች ዝዉዉር ላይ መሳተፍ አለመቻሉ ታዉቃል።
ለአንድ ተጫዋች በመቶ ሺዎች በሚከፈልበት ሊግ የክለቡ አመራሮች 45 ሺ ብር ደመወዝ ብቻ ለመክፈል መዘጋጀታቸዉ አስገራሚ ሲሆን ክለቡም ከአሁኑ የፋይናስ ችግር ዉስጥ መግባቱን አመላካች ሆኗል ።
የለገ ጣፎ ለገዳዲ እግር ኳስ ክለብን ለማጠናከር ባለሃብቱን ተሳታፊ ባደረገ መልኩ ብዙ ስራ ለመስራት ቃል ቢገባም በቂ ስራ ባለመሰራቱ አይደለም አዲስ ተጫዋች ለማስፈርም ከከፍተኛ ሊግ አብረዉት ያደጉትን ተጨዋቾች እንኳን ኮንትራት ለማራዘም መቸገሩ ታዉቃል ።
የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ጥላሁን የ8 ተጨዋቾችን ኮንትራት ለማራዘም እንደሚፈልግ እና አዳዲስ ተጨዋቾችን ወደ ክለቡ ለመቀላቀል ቢንቀሳቀስም የተጨዋቾች የዋጋ ንረት ከክለቡ አነስተኛ በጀት ጋር ተደምሮ ከፍተኛ ችግር እንደፈጠረበት ገልጿል ።
- ማሰታውቂያ -
ክለቡ ለተጨዋቾች ቃል የገባዉን ሽልማት ጨምሮ ሌሎች ኢንሴቲቮችን አለመክፈሉም በተጨማሪነት ታዉቋል ።