ቀን 10:00 ሰዓት ሲል በኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ አሸብር ሰቦቃ ፊሽካ በጀመረዉ እና በእንቅስቃሴ ረገድ ቀዝቃዛ በነበረዉ የዕለቱ ጨዋታ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ላይ አፄዎቹ በኳስ ቁጥጥር ተሽለዉ ሲንቀሳቀሱ ፤ በተቃራኒው ሲዳማዎች ደግብ በአብዛኛው ወደ መስመር በሚላኩ ረዣዥም ኳሶች አደጋ ለመፍጠር ሲጥሩ ተስተዉሏል። በዚህ ሂደት በቀጠዉ ጨዋታም ሲዳማዎች በና በ12ተኛዉ ደቂቃ ላይ ሙከራ ማድረግ ችለዋል ፤ በዚህም ይገዙ ከበዛብህ የተሻገረለትን ኳስ ይገዙ ቦጋለ እየገፋ ወደ ሳጥኑ ጠርዝ ከደረሰ በኋላ ኳሷን አክርሮ ወደ ግብ ልኳት የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ኳሷ በግቡ ቋሚ ለጥቂት ወደ ዉጭ ወጥታለች።
ቃልኪዳን በቀኝ መስመር በኩል ከአቤል እንዳለ በአንድ ሁለት ቅብብል ያገኛትን ኳስ ሳጥን ዉስጥ ደርሶ በቀጥታ ወደ ግብ ቢሞክርም ኳሷ ወደ ዉጭ ወጥታለች ። በተጨማሪም በአማካዩ ጋቶች ፓኖም እና ቃልኪዳን ዘላለም አማካኝነት ሌሎች እድሎችን መፍጠር የቻሉት አፄዎቹ አጋማሹ ሊገባደድ በጣት የሚቆጠሩ ደቂቃዎች በቀሩበት ወቅት ግን ግብ ተቆጥሮባቸዋል ። በዚህም በ44ተኛዉ ደቂቃ ላይ ከእዮብ የተቀበለዉን ኳስ የግብ ዘቡ ይድነቃቸው መቆጣጠር አለመቻሉን ተከትሎ አጠገቡ የነበረዉ ማክል ኪፕሮል ኳሷን ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል።
ከግቧ መቆጠር ከሁለት ደቂቃ በኋላ ግን ፋሲሎች ወዲያዉኑ የአቻነት ግብ ማስቆጠር ችለዋል ፤ በዚህም ቃልኪዳን ዘላለም ከአቤል እንዳለ የተሻገረለትን የአየር ላይ ኳስ ከተቆጣጠረ በኋላ በፍጥነት ኳሷን በሚገርም ሁኔታ ከሳጥኑ ጠርዝ ላይ ወደ ግብነት በመቀየር አጋማሹ ሳይጠናቀቅ ክለቡን አቻ ማድረግ ችሏል።
- ማሰታውቂያ -
ከዕረፍት መልስ በእንቅስቃሴ ረገድ ይበልጥኑ ተሽለዉ የተመለሱት አፄዎቹ በ48ተኛዉ ደቂቃ ድንቅ የግብ ዕድል መፍጠር ችለዉ ነበር ፤ በዚህም አጥቂዉ ጌታነህ ከኤልያስ ማሞ የተቀበለዉን ኳስ ወደ ግብ ቢሞክርም ግብ ጠባቂዉ መክብብ ኳሷን ይዟታል። በድጋሚ በ62ተኛዉ ደቂቃ ላይ ቃልኪዳን ዘላለም ከአቤል የተቀበለዉን ኳስ ወደ ግብ ሞክሮ ኳሷ ስትወጣ ፤ ሲዳማ ቡናዎችም በይገዙ ቦጋለ እና በጋናዊዉ አጥቂ አማካኝነት ሁለት ድንቅ ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዉ ነበር ።
በዚህ ሂደት በቀጠለዉ ጨዋታ በ64ተኛዉ ደቂቃ ላይ ከቀኝ በኩል የተገኘዉን ቅጣት ምት ተከላካዩ አምሳሉ ጥላሁን በቀጥታ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን መሪ ማድረግ ችሎ የነበረ ቢሆንም ፤ ከሶስት ደቂቃዎች በኋላ ግን ሲዳማዎች የአቻነት ግብ አግኝተዋል በዚህም አጥቂዉ ማይክል ኪፕሩል ከቀኝ ጠርዝ በቀጥታ ወደ ግብ የላካት ኳስ ወደ ግብነት ተቀይራ የሁለቱ ክለቦች የቀኑ መርሐግብር ሁለት አቻ በሆነ ዉጤት ፍፃሜዉን አጊኝቷል።
* በዕለቱ ሁለተኛ መርሐግብር ወላይታ ዲቻ ኢትዮጵያ መድንን ሁለት ለአንድ በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል ።
ያን ያህል ተጠቃሽ ሙከራ ባልተመለከትንበት እና ደብዛዛ በነበረዉ የምሽቱ ጨዋታ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ላይ ወላይታ ዲቻዎች በአንፃራዊነት የጨዋታ ብልጫ ወስደዉ ረዣዥም ኳሶችን ወደ ፊት መስመር በመላክ እና በፈጣን ሽግግር እድሎችን ለመፍጠር ሲጥሩ ፤ በተቃራኒው መድኖች ደግሞ በአንድ ሁለት የጨዋታ ቅብብል ወደ ሳጥን ከደረሱ በኋላ እድሎችን ፈጥረዉ ግብ ለማስቆጠር ሲንቀሳቀሱ የተስተዋሉት መድኖች ገና በመባቻዉ አቡበከር ሳኒ ያሻገራትን ኳስ ተከላካዩ አንተነህ ሲጨርፋት ያገኛት አብዲሳ ጀማል ወደ ግብ ሞክሯት ለጥቂት ወጥታለች።
ከዚች ሙከራ በኋላ እምብዛም ለዕይታ ማራኪ ባልነበረዉ የመጀመሪያዉ አጋማሽ በ34ተኛዉ ደቂቃ ላይ አብዲሳ ጀማል ናትናኤል ናሲሩ ላይ ጥፋት መስራቱን ተከትሎ በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግዷል። ከዕረፍት መልስ በተመሳሳይ የጨዋታ እንቅስቃሴ በቀጠለዉ የምሽቱ መርሐግብር በ54ተኛዉ ደቂቃ ላይ የጦና ንቦቹ መሪ መሆን የቻሉበትን ግቦች አግኝተዋል። በዚህም የመድን ተከላካዮች የሰሩትን ስህተት ተጠቅሞ ብስራት በቀለ ያገኛትን ኳስ የግብ ዘቡን አቡበከር ኑራ በማለፍ ድንቅ ጎል አስቆጥሮ ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል።
ግብ ከተቆጠረባቸዉ በኋላ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ቀይረዉ ወደ ሜዳ ያስገቡት መድኖች ከተደጋጋሚ ሙከራዎች በኋላ ተሳክቶላቸው የአቻነት ግብ አግኝተዋል። በዚህም በ72ተኛዉ ደቂቃ ላይ እዮብ ተስፋየ ብሩክ ሙሉጌታ ላይ የሰራዉን ስህተት ተከትሎ የተሰጠዉን ፍፁም ቅጣት ምት አሚር ሙደሲር አስቆጥሮ ጨዋታዉን አቻ ማድረግ ችሏል።
የጨዋታዉ ደቂቃ እየገፋ በሄደ ቁጥር ግለቱ በተፋፋመዉ ጨዋታ በ81ኛዉ ደቂቃ ላይ ዲቻዎች ዳግም መሪ መሆን ችለዋል ፤ በዚህም ከዘላለም ኢሳያስ የተቀበለዉን ኳስ ብስራት በቀለ ወደ ግብነት ቀይሮ መድን ሁለት ለአንድ መምራት ሲጀምር ፤ ጨዋታዉ ተጠናቀቀ ተብሎ የዳኛዉ ፊሽካ ሲጠበቅ ግን መሐመድ አበራ የአቻነት ገብ አስቆጥሮ ጨዋታዉ 2ለ2 በሆነ ዉጤት ተጠናቋል