በዚህም 75ኛው ደቂቃ ላይ የኢትዮ ኤሌክትሪክ ተከላካዮች የሰሩትን ስህተት ተጠቅሞ ኳሱን ያገኘው አዲሱ ፈራሚ ዱሬሳ ሹቢሳ ኳስ እና መረብን በማገናኘት በባህርዳር ከተማ አጀማመሩን አሳምሯል ።
በደጋፊዎቻቸው ከፍተኛ ድጋፍ እያገኙ የነበሩት የጣና ሞገዶቹ በቀጣዮቹ ደቂቃዎች ላይ የማሸነፊያ ግብ ለማግኘት ሲጥሩ በኢትዮ ኤሌክትሪክ በኩልም በተወሰኑ አጋጣሚዎች ጥሩ ጥሩ የግብ አጋጣሚዎችን ለመፍጠር ችለዋል ።
በተለይም ተቀይሮ የገባው ሄኖክ ኢሳይያስ በ79ኛው ደቂቃ ላይ ከሳጥኑ ወደ ግራ ካደላ ቦታ ላይ ያገኘውን የቅጣት ምት በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ የግቡ አግዳሚ የመለሰበት ኳስ ለአሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተናው ቡድን አስቆጪ ነበር ።
- ማሰታውቂያ -
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሊጠናቀቅ ሶስት ያህል ደቂቃዎች ብቻ ሲቀሩት ግን ግብ ተቆጥሮባቸውል ። በተጠቀሰው ደቂቃ ላይ ከማዕዘን የተሻማን ኳስ ተስፋዬ ታምራት በግንባር ገጭቶ በማስቆጠር የጣና ሞገዶቹ ከመመራት ተነስተው ማሸነፍ እንዲችሉ አድርጓል ።
በሁለተኛው ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው ረቡዕ መስከረም 25 ቀን 7:00 ላይ ባህርዳር ከተማ ከወልቂጤ ከተማ ሲጫወቱ በተከታዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚገጥም ይሆናል ።