የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ባህርዳር ከተማን ከሀድያ ሆሳዕና አገናኝቶት ተከላካዩ ፍሬዘር ካሳ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ሀድያ ሆሳዕናዎች አሸንፈው መውጣት ችለዋል ።
ባህርዳር ከተማ በ16ኛው ሳምንት ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ላይ ከነበረው ምርጥ 11 ስደስት ለውጦችን በማድረግ ወደ ሜዳ የገቡ ሲሆን ኡቡበከር ኑሪ ፣ ሰለሞን ወዴሳ ፣ መሳይ አገኘሁ ፣ በረከት ጥጋቡ ፣ ፍፁም አለሙ እና አሊ ሱሌማን በፋሲል ገብረሚካኤል ፣ መናፍ ዓወል ፣ አህመድ ረሺድ ፣ አለልኝ አዘነ ፣ ተመስገን ደረሰ ፣ ኦሴ ማውሊን በአሰላለፍ ያካተቱ ሲሆን ሀድያ ሆሳዕና ደግሞ ከፋሲል ከተማ ጋር ነጥብ በተጋሩበት ጨዋታ ጨዋታ ከነበረው ቋሚ አሰላለፍ ሁለት ቅያሪዎችን በማድረግ የገቡ ሲሆን ያሬድ በቀለን እና ግርማ በቀለን በሶሆሆ ሜንሳህ እና ሳምሶን ጥላሁን ተክተዋል ።በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ባህርዳር ከተማዎች አንፃራዊ ብልጫን በመውሰድ ያሳለፉበት ነበር ። በሁለተኛው ደቂቃ ላይም ገና በጊዜ መሪ መሆኖ የሚችሉበትን ዕድሎ ቢያገኙም ሊጠቀሙበት ሳይችሉ ቀርተዋል ። በአጋጣሚው ኦሴ ማውሊ በግራ አቅጣጫ ወደ ሳጥን ይዞ የገባውን ኳስ ነፃ ለነበረው ተመስገን ደረሰ ቢያቀብለወም በማይታመን መልኩ ተመስገን ኳሱን ሳይጠቀምበት ቀርቷል ።
ባህርዳር ከተማዎች ብልጫ ወስደው አደገኛ የግብ ዕድሎችን መፍጠር ቢችሉም ኳስ እና መረብን ማገናኘት አልቻሉም ። በአንፃረለ በተወሰደባቸው ብልጫ ወደ ኋላ አፈግፍገው የነበሩት ሀድያ ሆሳዕናዎች ከውሀ እረፍት መልስ በተወሰነ መነቃቃት ወደ ፊት በማለፍ የባህር ዳር ከተማን የኋላ መስመር ለመፈተን ሞክረዋል ። በዚህም 34ኛው ደቂቃ ላይ ግብ አስቆጥረዋል ።አበባየሁ ዮሀንስ ከማዕዘን ያሻገረውን ኳስ የባህርዳሩ ግብ ጠባቂ ፋሲል ገብረሚካኤል ኳሱን ለማራቅ ሞክሮ ሊደርስበት ሳይችል ሲቀር ከጀርባው የነበረው ፍሬዘር ካሳ በግንባር በመግጨት ሀድያን መሪ ያደረገ ግብ አስቆጠረ ። የመጀመሪያው አጋማሽም በሀድያ ሆሳዕና የ1 – 0 መሪነት ተጠናቀቀ ።
በሁለተኛው አጋማሽ ባህርዳር ከተማዎች በተጣባባቂ ወንበር ላይ ያሉ የማጥቃት ባህሪ ያላቸውን ተጫዋቾች ቀይረው በማስገባት ግብ ለማግኘት ጥረቶችን ያደረጉ ሳሆን በአጋማሹም ከፍተኛ የበላይነት ነበራቸው ። በሃድያ ሆሳዕና በኩል በመከላከሉ ላይ ትኩረት አድርገው አልፎ አልፎ በፈጣን ኳሶች ወደ ባህርዳር ከተማ የግብ ለመድረስ ሞክረዋል ።
- ማሰታውቂያ -
በአጋማሹ ባህር ዳር ከተማዎቾ በኳስ ቁጥጥሩ ብለጫ ቢወስዱም ጥሩ የሚባል የግብ ዕድል መፍጠር የቻሉት ግን ሀድያ ሆሳዕናዎች ናቸው ። በ64ኛ ደቂቃ ላይ ሀብታሙ ታደሰ በጥሩ ቅብብል ዘደ እሱ የደረሰውን ኳስ ወደ ግብ መሞከር ቢችልም የግቡ ቋሚ መልሶበታል ።
ባህርዳር ከተማዎች የአቻነቷን ግብ ለማግኘት ከመስመር በሚነሱ እና ከቆሙ ኳሶች የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር ቢሞክሩም ውጤታማ አልነበሩም ።
በ83ኛው ደቂቃ ላይ ከቅጣት ምት የተሻማውን ኳስ ግብ አስቆጣሪው ፍሬዘር ካሳ የፃ ሆኖ ማግኘት ቢችልም በግንባር የገጨው ኳስ ኢላማውን ሳይጠብቅ ወደ ውጪ ወቷል ።
በመጨረሻም በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት የሚመራው ሀድያ ሆሳዕና 1 – 0 በማሸነፍ ደረጃውን ማሻሻል ችሏል ።
ውጤቱን ተከትሎ ሀድያ ሆሳዕና ነጥቡን 21 በማድረስ 9ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ባህርዳር ከተማ በበኩሉ በተመሳሳይ 21 ነጥብ በግብ ክፍያ በልጦ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ።
በ18ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው ሀሙስ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ባህርዳር ከተማ ወልቂጤ ከተማን ሲገጥም ሀድያ ሆሳዕና በበኩሉ በመጪው ሰኞ ቀን 9 ሰዓት ላይ ከአርባ ምነጭ ከተማ ጋር የሚጫወት ይሆናል ።