በዉጤት ደረጃ በተለይ ለአዲስ አበባ ከተማዎች ወሳኝ በነበረዉ የምሳ ሰዓቱ ጨዋታ አዲስ አበባ ከተማ ወላይታን በቡዙአየሁ ብቸኛ ግብ ማሸነፍ ችላል።
ከጨዋታው ጅማሮ አንስቶ በእንቅስቃሴ ደረጃ የተቀዛቀዘ የነበረዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ እምብዛም ለተመልካች ማራኪ ነበር ለማለት ያስቸግራል፤ በተለይ ካሉበት ደረጃ አንፃር የወላይታ ድቻዎች የበላይነት ይኖራል ተበሎ ቢጠበቅም በተቃራኒው አዲስአበባ ከተማዎቾ በእንቅስቃሴ ደረጃ ተሽለዉ ወደ ተቃራኒ የግብ ክልል ለመድረስ ሲንቀሳቀሱ ተስተውለዋል።
በዚህ ሂደት በቀጠለዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታም በ32ኛዉ ደቂቃ ላይ ከማዕዘንት ምት የተሻገረዉን ኳስ ሪችሞንድ አዶንጎ ወደ ግብ ምክሮ የነበረ ቢሆንም ኳሱ ኢላማዉን ሳይጠብቅ ወደ ወጭ ወጥቷል። ከደቂቃዎች በኋላ በድጋሚ ፍፁም አስፋዉ ከቀኝ መስመር ተከላካዩ የተሻማዉን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ግብ ለማስቆጠር ቢሞክርም በተመሳሳ ኳሷ በግቡ አናት ላይ ወጥታለች።
- ማሰታውቂያ -
ምንም እንኳን ኢላማዉን የጠበቀ ባይሆንም የመጀመሪያዉን የግብ ሙከራ ለማድረግ 32 ደቂቃዎች በፈጁበት በዚህ ጨዋታ ላይ በሁለቱም ክለቦች በኩል በተመሳሳይ በመሀል ሜዳዉ ላይ የተሻለ ብልጫ ለመዉሰድ ሲታትሩ የተመለከትንም ቢሆን በአብዛኛው ከሚቆራረጡ ቅብብሎች ዉጭ ተጠቃሽ አስደንጋጭ ሙከራ ሳንመለከትበት የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።
ከአጋማሹ መልስ በተመሳሳይ የጨዋታ ሂደት የቀጠለዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታም በሂደት መነቃቃት እየታየበት ቢመጣም በሙከራ ረገድ ግን ጠንከራ ያለ ነገርን የመለከትነዉ በ58ኛዉ ደቂቃ ላይ ነበር፤ በዚሁ ሰዐት ሪችሞንድ አዶንጎ ከቀኝ መስመር በኩል የተቀበለዉን ኳስ አክርሮ ወደ ግብ ቢልካትም ግብ ጠባቂዉ ቢንያም እንደምንም አዉጥቷታል።
በ70ኛዉ ደቂቃ ላይ ደግሞ በግራ መስመር በኩል እንዳለ ከበደ ያሻገረዉን ኳስ አጥቂዉ ሪችሞንድ በጭንቅላቱ ገጭቶ ቢሞክርም ግብ ጠባቂዉ ቢኒያም ተቀላሉ ተቆጣጥሯታል።በተቃራኒዉ በወላይታ ዲቻ በኩል ደግሞ 82ኛዉ ደቂቃ ላይ ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባዉ እንድሪስ ሰይድ ከርቀት አክሮሮ የሞከራት ኳስ ቅንድ የነበረች ቢሆንም ግብ ጠባቂዉ ዳንኤል ተሾመ ከዉጥቶበታል።
ካለቡት ደረጃ እና ከዚህ ቀደም ከነበሯቸዉ ጨዋታዎች በመነሳት በተደጋጋሚ በጨዋታዉ መገባደጃ ሰዓት ላይ ይቆጠሩባቸዉ የነበሩትን ግቦች ለመቅረፍ በሚመስል መልኩ የጨዋታዉ ሰዓት እየገፋ በመጣ ቁጥር ይበልጥ ጥንቃቄ የታከለበት የጨዋታ ሂደትን ሲከተሉ የተስተዋሉ የነበሩት አዲስአበባ ከተማዎች በጨዋታው መገባደጃ በ90ኛዉ ደቂቃ ላይ አሸናፊ ያደረገቻቸዉን ግብ ተቀይሮ በገባው ብዙአየሁ ሰይፈ አማካኝነት አስቆጥረዋል። በዲቻዎች የግብ ክልል አካባቢ የተገኘዉን ቅጣት ምት አሰጋኸኝ ጴጥሮስ ሲመታዉ ተደርቦ የተመለሰዉን ኳስ ብዙአየሁ አግኝቶ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡ አዲስአበባ ከተማ ጣፋጭ ሶስት እንዲያገኝ አስችሏል።
ዉጤቱን ተከትሎ አዲስ አበባ ከተማ በ28 ነጥብ አስራ አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በአንፃሩ ወላይታ ድቻ ደግሞ በ37 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።