በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ይገኙ የነበሩት ሁለቱ ክለቦች ጨዋታቸዉን በወጣላቸው መርሀግብር መሰረት እኩለ ቀን 7:00 ሲል በጀመረው ጨዋታ ተመጣጣኝ የሚባል የኳስ ፍሰት በተመለከትንበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በጅማ አባጅፋር በኩል ወደ መስመር ያተኮረ የአጨዋወት መንገድን ለመተግበር ሲሞክሩ የታዘብን ሲሆን በአንፃሩ ሀምበሪቾ ዱራሜዎች ደግሞ በመሀል ተጫዋቾቻቸዉ ፀጋአብ ዩሴፍ እና ሮቦት ሰለሞን ወደፊት ለመሄድ ጥረት ሲያደርጉ ተመልክተናል።
ጅማ አባጅፋሮች በተደጋጋሚ ረጃጅም ኳሶችን ወደ መስመር በመጣል ወደ ተጋጣሚ ቡድን የግብ ክልል ለመድረስ የሚያደርጉት ጥረት እንዳለ ሆኖ ለጥንቃቄ በሚመስል መልኩ ተከላካዮቹን ይበልጥ በመጠቅጠቅ የተቃራኒ ቡድንን የማጥቃት አቅም ሲያዳክሙ እና ሲያከሽፋም ተመልክተናል።
- ማሰታውቂያ -
ተጋጣሚዉ ሀምበሪቾም አልፎ አልፎ ከሚያደርጓቸው ሙከራወች በዘለለ በደንብ ወደፊት ገፍተዉ በመጫዎት ጫና ለማድረግ በማሰብ በአንድ ሁለት ቅብብሎሽ ወደ ጅማ የግብ ክልል ለመድረስ የሚያደርጉት ጥረት ዉጤታማ አልነበረም።
ከእረፍት መልስ ገና ጨዋታዉ እንደተጀመረ በእለቱ ድንቅ ሲንቀሳቀስ የነበረዉ አማካዩ ንጋቱ ገ/ስላሴ በ46′ ደቂቃ ግሩም ግብ አስቆጥሮ ጅማ አባጅፋርን መሪ ማድረግ ቻለ።
ከግቡ መቆጠር በኋላ ሁለቱ ቡድኖች በእንቅስቃሴ ረገድ ተቀዛቅዘዉ ጨዋታቸዉን በዚሁ ዉጤት አጠናቀዋል።
ደረጃ ሰንጠረዥና ቀጣይ መርሐግብር