በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ሁለቱ መቀመጫቸውን በሀዋሳ ያደረጉትን ሲዳማ ቡናን እና ሃዋሳ ከነማን አገናኝቶ ሲዳማ ቡና 3 – 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል ።
ሲዳማ ቡና በ17ኛው ሳምንት ከድሬዳዋ ከተማ ነጥብ በተጋሩበት ጨዋታ ላይ ከነበረው ቋሚ አሰላለፍ ሁለት ለውጦችን በማድረግ ሙሉአለም መስፍንን እና ሳልሀዲን ሰይድን በብርሀኑ አሻሞ እና በብሩክ ሙሉጌታ ተክተወሰ ሲገቡ በሀዋሳ ከነማ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ከወላይታ ድቻ አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ከነበረው ምርጥ 11 ሁለት ቅያሪዎችን በማድረግ ዳግም ተፈራን እና አብዱልባሲጥ ከማልን በመሀመድ ሙንታሪ እና ወንድማገኝ ሀይለለ ምትክ አሰልፈዋል ።የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ በአብዛኛው የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ሲዳማ ቡና የበላይ ሆነው የታዩበት ነበር ። በዚህም ገና በ9ኛው ደቂቃ ላይ ከማዕዘን ምት በተነሳ ኳስ በሙሉአለም መስፍን አማካኝነት ቀዳሚ መሆን ችለዋል ።ከፊት መስመር ላይ በውድድር አመቱ ጥሩ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘውን ይገዙ ቦጋለን እና አናጋፋውን አጥቂ ሳልሀዲን ሰይድን ያሰለፉት ሲዳማ ቡናዎች ቀዳሚ ከሆኑ በኋላም ሌላ ተጨማሪ ግብ ለማስቆጠር ጥረቶችን አድርገዋል ። በ17ኛው ደቂቃ ላይም የሲዳማ ቡናው ተከላካይ ጊት ጋትኩት ከማዕዘን የተሻገረን ኳስ በግንባር ገጭቶ ለማስቆጠር ቢሞክርም ዳግም ተፈራ አድኖበታል ።
በአጋማሹ ከፍተኛ ብልጫ የተወሰደባቸው ሀዋሳ ከተማዎች በ11ኛው ደቂቃ ላይ በመስፍን ታፈሰ አማካኝነት ወደ ግብ የላኩት ኳስ በተክለማርያም ሻንቆ ግብ ከመሆን ድኗል ።
በተደጋጋሚ ወደ ተጋጣሚያቸው የግብ ክልል መድረስ የቻሉት ሲዳማ ቡናዎች በ28ኛው ደቂቃ ላይ በሳልሀዲን ሰይድ አማካኝነት ያደረጉት ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ በግብ ጠባቂው ዳግም ተፈራ ተመልሷል ።በ38ኛው ደቂቃ ላይ ግን የሲዳማ ቡና ተከላካዮች መዘናጋት ግብ እንዲያስተናግዱ አድርጓቸዋል ። ፀጋሰው ድማሙ ከግብ ክልሉ በረጅም የመታውን ኳስ ያገኘው መስፍን ታፈሰ የሲዳማ ቡና ተከታለካዮችን አምልጦ በመግባት በተክለማርያም ሻንቆ መረብ ላይ በማሳረፍ ሀይቆቹን አቻ አድርጓል ። የመጀመሪያው አጋማሽም በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ ።በሁለተኛው አጋማሽ ሽኩቻዎች ጥፋቶች የበዙበት ሆኖ ያለፈ ሲሆን ሀዋሳ ከተማዎች በመጀመሪያዎቹ የአጋማሹ ደቂቃዎች ላይ በተሻለ ወደ ፊት ማለፍ ቢችሉም የጠራ የግብ ዕድል ለመፍጠር ተስኗቸው ነበር ። በአንፃሩ በመጀመሪያው አጋማሽ በነበራቸው ብልጫ መቀጠል ያልቻሉት ሲዴማ ቡናዎች በ65ኛው ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ግብ በማስቆጠር ዳግም መሪ መሆኖ ችለዋል ። ዳዊት ተፈራ ከመለል ለሳልሀዲን ሰይድ ያቀበለው ኳስ ይገዙ ጋር ደርሶ አጥቂው ወደ ሳጥን ይዞ የገባው ኳስ በዳግም ተፈራ ሲመለስ ያገኘው ዳዊቴ ተፈራ ኳሱን አንድ ጊዜ ከገፋ በኋላ በሀዋሳ ከተሣ መረብ ላይ አሳርፎታል ።ጥፋቶች በበዙበት የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 77ኛው ደቂቃ ላይ የሲዳማ ቡናወሰ አምበል ፍሬው ሰለሞን በዳንኤል ደርቤ ላይ በሰራው ጥፋት የሁለተኛ ቢጫ ካሬድ ተመልክቶ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል ።መደበኛው የጨዋታ መጠናቀቂያ ደቂቃ ላይ ሀዋሳ ከነማዎች ያገኙትን የማዕዘን ምት ለመጠቀም ሲጥሩ ሲዳማ ቡናዎች ቀምተው በፈጣን መልሶ ማጥቃት ወደ ፊት በማለፍ በይገዙ ቦጋለ አማካኝነት ሶስተኛ ግብ አስቆጥረ። ጨዋታውም በሲዳማ ቡና የ3 – 1 አሸናፊነት ተጠናቀቀ ።ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና ነጥቡን 30 ማድረስ ቢችልም በደረጃው ላይ ለውጥ ሳያደርግ 5ኛ ላይ የቆየ ሲሆን በአንፃሩ ሀዋሳ ከነማ በ31 ነጥብ ወደ 4ኛ ደረጃ ዝቅ ብሏል ።
- ማሰታውቂያ -
በ19ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሲዳማ ቡና በመጪው ዕሁድ አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ ከሰበታ ከተማ ሲጫወት ሀዋሳ ከተማ ደግሞ በመጪው ረቡዕ ቀን 9 ሰዓት ላይ ወልቂጤ ከተማን ይገጥማል ።