ተጠባቂውን የደርቢ ጨዋታ ወላይታ ድቻ አርባምንጨሰ ከተማን በምንይሉ ወንድሙ ብቸኛ የፍፁም ቅጣት ምት ግብ አሸንፈው ወተዋል ።
ወላይታ ድቻ በዘጠነኛው ሳምንት በሲዳማ ቡና ሲሸነፉ ከተጠቀሙት ቋሚ አሰላለፍ ስንታየሁ መንግሥቱን እና መልካሙ ቦጋለን በምንይሉ ወንድሙ እና አንተነህ ጉግሳ ሲኩ አርባምንጭ ከተማዎች በሀዋሳ ከተማ በተረቱበት ጨዋታ ከነበረው ቋሚ አሰላለፍ ሶሰትትፈ ቅያሪዎችን በማድረግ በሙና በቀለ ፤ አንዱአለም አስናቀ እና መላኩ ኤልያስ ምትክ ወርቅይታደስ አበበ ፤ አቡበከር ሻሚል እና አሸናፊ ኤልያስን ተከተው አስገብተዋል ።
የጨዋታ የመጀመሪያ አጋማሽ ጥሩ ፉክክር የታየበት ኳሶች ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ ክልል የሚደርሱበች ነበር ምንም እንኳን ኢላማቸውን የጠበቁ የግብ ሙከራዎችን እምብዛም ባንመለከትም ።
- ማሰታውቂያ -
በወላይታ ድቻ በኩል ሰብረው ወደ ፍፁም ቅጣች ምት ሳጥን ውስጥ በመግባት እና ከቅጣት ምቶች ዕድሎችን ለመፍጠር ጥረቶችን ያደረጉ ሲሆን በአርባምንጭ ከተማ በኩል ደግሞ ከፊት መስመር ባሉ ተጫዋቾቻው ወደ ሶሰትኛው የማጥቃት ዞን ለመግባች የሚያደርጉት ጥረት በቀላሉ በወላይታ ድቻ የተከላካይ ክፍል ይነጠቁ ነበር ። ሀቢብ ከማል 29ኛ ደቂቃ ላይ ከርቀት ከሞከረው እና ኢላማውን ከሳተው ኳስ ውጪ በአዞውቹ በኩል የተደረገ ጠንካራ የግብ ሙከራ ያልነበረ ሲሆን በጦና ንቦቹ በኩል ደግሞ በተለይም በእድሪስ ሰዒድ አማካኝነት የተደረጉ የግብ ሙከራዎች ወደ ውጪ በመውጣት እና በግብ ጠባቂው በመያዝ ግብ መሆን አልቻሉም ።
የሁለተኛው አጋማሽ በጥሩ የማጥጣፍላጎት የቀጠለ ሲሆን በአንፃራዊነት የአርባምንጭ ከተሣ የበላይነት የተስተዋለበት ነበር ። ነገር ግን የግብ ሙከራዎች ለመመልከት ደቂቃዎችን መጠበቅ የግድ ብሎ ነበር ።
በአጋማሹ 63ኛ ደቂቃ ላይ አርባምንጭ ከተማዎች ጥሩ ዕድልን አግነኝተው ነበር ። የወላይታ ድቻው ግብ ጠባቂ ወንደወሰን አሸናፊ የሰራውን ስህተት ተከትሎ ኳሱን ያገኘው ፀጋዬ አበራ አስቆጠረው ተብሎ ሲጠበቅ ግብ ሳያደርገው ቀርቷል ።
የማጥቃት ብልጫው የተወሰደባቸው ወላይታ ድቻዎች 66ኛ ደቂቂ ላይ በፈጣን እንቅስቃሴ ያገኙትን ዕድል በያሬድ ዳዊት አማካኝነት ወደ ግብ ቢሞክሩም በግብ ጠባቂው ተመልሶበታል ። ከአንድ ደቂቃ በኋላ ደግሞ ከማዕዘን የተሻገረውን ኳስ ምንይሉ ወንድሙ በግንባር ገጭቶ የግቡ አግዳሚ መልሶበታል ።
ያለምንም ግብ የቀጠለው ጨዋታ 72ኛ ደቂቃ ላይ ሲደርስ ግን ኳስ ከመረብ ተገናኝቷል ። በረጅም የተማን ኳስ ተፍቶት የነበረው የአርባ ምንጩ ግብ ጠባቂ ይስሀቅ ተገኝ ኳሱን በድጋሚ ለመያዝ ባደረገው ጥረት ምንይሉ ወንድሙ ላይ ጥፋት መስራቱን ተከትሎ የጦና ንቦቹ ያገኙትን የፍፁም ቅጣት ምት ጥፋቱ የተሰራበት ተጫዋች አስቆጥሮ መሪ መሆን ችለዋል ።
በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይ ወላይታ ድቻዎች ወደ ኋላ አፈግፍገው በመጫወት ውጤቱን አስጠብቀው መውጣት ችለዋል ። ወላይታ ድቻም ከሶሰት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ያሸነፈው ጨዋታ ሆኗል ።
ውጤቱን ተከትሎም የጦና ንቦቹ ነጥባቸውን ወደ 16 በማሳደግ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ ሲሉ በአንፃሩ አዞዎቹ በ11 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።