የመቻል እግር ኳስ ቡድን በተጠናቀቀው የውድድር አመት የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች የነበሩትን አጥቂውን ምንይሉ ወንድሙ የግራ መስመር ተከላካይ ዳዊት ማሞ እና መሀል ተከላካዩን ነስረዲን ሀይሉን ውል ለተጨማሪ አንድ አመት አራዝሟል።
አጥቂው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት 15 ጎሎችን በማስቀጠር የሊጉ ሁለተኛ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ የጨረሰው ምንይሉ ወንድሙ ከመቻል ጋር ለተጨማሪ አንድ አመት ለመቆየት ፈርሟል።
ሁለተኛው በመቻል ቤት ታመኙ ተጫዋች በመባል እና መቻል ወደ ከፍተኛ ሊግ ሲወርድ አብሮ በመውረድ ለክለቡ ታማኝነቱን ያሳየው የግራ መስመር ተመላላሹ ዳዊት ማሞ ሌላኛው ለመቻል ውሉን ያራዘመ ተጫዋች ሆኗል።
ሶስተኛው የመሀል ተከላካዩ ነስረዲን ሀይሉ ሲሆን በተጠናቀቀው የውድድር አመት አስቻለው ታመነ በጉዳት ከጨዋታ በራቀባቸው ጊዜ ከጋናዊው አስቴቨን ባዱ ጋር ምርጥ ብቃቱን በማሳየት ለቡድኑ ጥሩ ግልጋሎት መስጠት የቻለውን ተከላካይ ለተጨማሪ ሁለት አመት ለማቆየት ተስማምቷል።
በተጨማሪ መቻል እግር ኳስ ክለብ የሌሎችን ነባር ተጫዋቾች ውል ለማራዘም በንግግር ላይ ይገኛል።