ባሳለፍነው የውድድር አመት ያጣውን የዋንጫ ክብር ለመመለስ በዝውውሩ በንቃት እየተሳተፈ የሚገኘው መቻል የሁለቱን ቁልፍ ተጫዋቾች የከነዓን ማርክነህ እና የበረከት ደስታን ውል ለተጨማሪ ሁለት አመት አራዝሟል።
በአዳማ ታዳጊ ቡድን ጅማሮውን አድርጎ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባለፉትን ሁለት አመት በመቻል ቤት ምርጥ ጊዜን ማሳለፍ የቻለው ከነዓን ማርክነህ ለተጨማሪ ሁለት አመት በክለቡ ለመቆየት በዛሬው እለት ተስማምቷል።
ሌላኛው የመስመር አጥቂው በረከት ደስታ ሲሆን የኳስ ህይወቱን የጀመረው በአዳማ ታዳጊ ቡድን አደርጎ በፋሲል ከነማ ምርጥ ጊዜን በማሳለፍ በ2015 ወደ መቻል በመምጣት ያለፉትን ሁለት አመታት በክለቡ የቆየ ሲሆን በትላንተናው እለት ለተጨማሪ ሁለት አመት በመቻል ለመቆየት ፈርሟል።