በአስረኛዉ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ቀን ሁለተኛ ጨዋታ የተገናኙት ኢትዮጵያ መድን እና ሀዋሳ ከተማ ጨዋታቸዉን 0ለ0 በሆነ አቻ ዉጤት አጠናቀዋል።
የሊጉን መሪነታቸውን በዘጠነኛው ሳምንት ለመዲናዉ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ አሳልፈዉ የሰጡት ኢትዮጵያ መድኖች የምሽቱን ጨዋታ በድል ተወጥተዉ ቢያንስ ቅዲስ ጊዮርጊስ እስከሚጫወት ድረስ ወደ መሪነት ይመለሳሉ ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቷል። እስከ አሁን ድረስ በሊጉ በቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ባህርዳር ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ብቻ ሽንፈትን ያስተናገዱት መድኖች ከጨዋታ ጨዋታ ራሳቸዉን በማሻሻል እና በሂደት እንደ ቡድን በጥንካሬ በመምጣት በደረጃ ሰንጠሰዡ አናት ላይ ከሚገኙ ክለቦች ተርታ ራሳቸዉን ማስቀመጣቸዉም አስደናቂ ጉዞ ሆኖ ተመዝግቦላቸዋል።
በተቃራኒው ወጥ የሆነ አቋም ከጨዋታ ጨዋታ ለማስመልከት እየተቸገሩ የመመገኙት ሀዋሳ ከተማዎች በቅርብ ሳምንታት እንደ ፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና የመሳሰሉ ክለቦችን መርታት ችለዉ የነበረ ቢሆንም በዘጠነኛዉ ሳምንት የሊጉ መርሐግብር ግን በቅዱስ ጊዮርጊስ ያልተጠበቀ የሶስት ለዜሮ ሽንፈት ማስተናገዳቸዉ ይታወሳል። በዚህም ከሽነፈት ለማገገም ወሳኝነቱ የላቀ በነበረዉ የምሽቱ ጨዋታ ከኢትዮጵያ መድን ጋር የጥብ ተጋርተዉ ወጥተዋል።
- ማሰታውቂያ -
ዉጤቱን ተከትሎም የገብረ መድህን ሀይሌዉ ኢትዮጵያ መድን በአንድ ነጥብ በልጦ መሪነቱ መረከብ ችሏል። በቀጣይ የሊጉ የአስራ አንደኛ ሳምንት መርሐግብርም ኢትዮጵያ መድን ከወልቂጤ ጋር ሲገናኙ ሀዋሳ ከተማ ደግሞ ከመቻል ጋር የሚጫወቱም ይሆናል።