ከአሰልጣኛቸዉ ዮሐንስ ሳህሌ ጋር ከተለየዩ በኋላ አዲሱን አሰልጣኛቸዉን በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርጉ የሚጠበቁት መከላከያዎች በዛሬዉ ዕለት ወደ ዝዉዉር ገበያዉ በመግባት ሁለት ተጨዋቾችን አስፈርመዋል።
የመጀመሪያ ፈራሚ በመሆን ጦሩን የተቀላቀለዉ የመስመር ተጫዋቹ በረከት ደስታ ሲሆን ከዚህ ቀደም ለአዳማ ከተማ መጫወት የቻለዉ እና ከ2012 ጀምሮ ደግሞ በአፄዎቹ ቤት ማሳለፍ የቻለዉ እና የሊጉን ዋንጫ ከፍ አድርጎ ማንሳት የቻለዉ በረከት ለሁለት አመታት በሚቆይ የስምምነት ዉል መከላከያን መቀላቀሉ ተረጋግጧል።
ሌላኛዉ ክለቡን የተቀላቀለዉ ደግሞ ቁመተ መለሎዉ የአማካፍ ስፍራ ተጫዋች ከንዓን ማርክነህ እንደሆነ ታዉቋል። ከዚህ ቀደም ለአዳማ ከተማ መጫወት የቻለዉ እና የዉድድር አመቱን ከፈረሰኞቹ ጋር ሻምፒዮን መሆን የቻለዉ ተጫዋቹ በዛሬዉ ዕለት በሁለት አመት በሚቆይ የኮንትራት ዉል ለመከላከያ መፈረሙ ተረጋግጧል።