የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ
(ታማኙና ተወዳጁ ጋዜጠኛ)
የእውቅና አሰጣጥ ስነ ስርዓት ዝግጅት
ረቂቅ ምክረ ሀሳብ
![](https://i0.wp.com/www.hatricksport.net/wp-content/uploads/2021/06/IMG_20210630_094436_682.jpg?resize=1080%2C1001&ssl=1)
ሰኔ 2013
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
- ማሰታውቂያ -
መግቢያ
ስፖርት በአለም አቀፍ ደረጃ በሰው ልጆች መካከል ፍቅርና ሰላም የሚፈጥርና ለሀገር እድገትም ከፍተኛ የሆነ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ሲሆን በውድድር ከሚገኝ ውጤትና ስኬት ባለፈ በየትኛውም እድሜ ክልል ቦታና የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎች ጤነኛ፣ ንቁና ውጤታማ እንዲሆኑ ይረዳል፡፡
ስፖርት ለአንድ ለተወሰነ አካል የሚተው ጉዳይ ባለመሆኑ በዙሪያው በርካታ ተዋናዮችን/ ባለድርሻ አካላትን የሚያሳትፍ ነው፡፡ እነዚህ ባለድርሻ አካላት ድርሻቸውን አውቀውና ተረድተው የሚያከናውኗቸው ተግባራት ድምር በስፖርት መስክ የሚገኘውን ውጤት ይወስነዋል፡፡ የስፖርት ጋዜጠኞች ከእነዚህ ባለድርሻ አካላት መካከል ሲሆኑ በሀገራችን ስፖርት ታሪክ በርካታ ለስፖርቱ የለፉና ሙያቸውን አክብረው አስተዋጽኦ ያበረከቱ ጋዜጠኞች አሉ፡፡ ጥሩ ስራን ማበረታታት ለሰራው ሰው እውቅና ከመስጠት ባለፈ ሌሎችንም ወደ ተመሳሳይ በጎ ነገር የሚያነሳሳ ነው፡፡
የእውቅና መስጠት መርሀግብሩ አላማ
በሀገራችን ስፖርት ላይ ትልቅ አሻራቸውን ካኖሩ ጋዜጠኞች መካከል ስራውን በመውደድ፣ ሙያዊ ስነ ምግባሩን በመጠበቅ፣ እሱ የሚፈልገውን ብቻ ሳይሆን ስፖርት ማህበረሰቡ የሚፈልገውን የስፖርት መረጃ በመዘገብና በማጠናቀር፣ በተልዕኮ ሳይሆን በርካቶች የማይገኙባው ቦታዎች ላይ በመገኘትና በሚዛናዊነት ለረጅም አመታት ከፍተኛ የሆነ ሙያዊ አስተዋጽኦ ያበረከተውን ታማኙንና ተወዳጁን ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴን ለሰራኸውና እየሰራህ ላለኸው ስራ እናመሰግናለን በማለት እውቅና መስጠት ነው፡፡
የእውቅና አሰጣጡ ወሰንና የሚሳተፉ አካላት
ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ በስፖርት ማህበረሰቡ ዘንድ በደንብ የሚታወቅና የሚወደድ በመሆኑ መላው የስፖርት ማህበረሰብ በእውቅና አሰጣጥ ስነ ስርዐቱ ላይ እንዲሳተፍ ሁኔታዎች ይመቻቻሉ፡፡ የእውቅና አሰጣጥ መርሀግብሩን የመሸሻ ወልዴ ምስጋናና እውቅና አሰጣጥ ኮሚቴ ከተለያዩ ኮሚሽኖች፣ ፌዴሬሽኖች፣ ኮሚቴዎች፣ ክለቦች፣ የተለያዩ ማህበራት (የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር፣ የፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማህበር፣ . . .)፣ የጤና ቡድኖች፣ ድርጅቶች፣ በአሁኑ ወቅት በስፖርት ላይ እየተሳተፉ ያሉና ቀደምሲል ሲሳተፉ የነበሩ አካላት፣ በአጠቃላይ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሚገኙ የስፖርት ቤተሰቦችና አላማውን የሚደግፉ ፍቃደኛ ስፖርት ወዳድ ግለሰቦችም የሚሳተፉበት ሁኔታ ይኖራል፡፡
የእውቅና አሰጣጥ መርሀግብሩ አካሄድ
የእውቅና አሰጣጥ መርሀግብሩ በሶስት ምዕራፍ ተከፍሎ የሚካሄድ ሲሆን የመጀመሪያው ምዕራፍ ስለ መሸሻ ወልዴ እውቅና አሰጣጥ የማስተዋወቅ ስራ የሚሰራበት የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ፣ ሁለተኛው ምዕራፍ እውቅናውን ለመስጠት የሚያስፈልገው የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ የሚሰራበት ሲሆን ሶስተኛውና የመጨረሻው ምዕራፍ የእውቅና አሰጣጡ የሚከናወንበት ምዕራፍ ነው፡፡
የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ
በቅድመ ዝግጅት ስራ ከሚከናወኑ ስራዎች መካከል ዋነኛው የመሸሻ ወልዴን የእውቅና አሰጣጥ መርሀግብር የማስተዋወቅ ስራ ነው፡፡ ይህ ስራ በሁሉም አማራጭ የህትመት፣ የኤሌክትሮኒክና (ሬዲዮና ቴሌቪዥንና በሌሎች የስፖርት ሚዲያዎች) በማህበራዊ ድረ ገጾችም የሚከናወን ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በፖስተሮች፣ በራሪ ወረቀቶችና በሌሎች አማራጮችም የማስተዋወቅ ስራው ይከናወናል፡፡
ምንም እንኳን ሁሉም ስፖርት ወዳድ ማህበረሰብ በእውቅና አሰጣጡ ላይ እንዲሳተፍ የሚፈለግ ቢሆንም በዋነኝነት የሚሳተፉ አካላትን (ድርጅቶችን፣ ግለሰቦችን፣ ባለሀብቶችን፣ . . .) የመለየት ስራ በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ እንዲሰሩ ከታቀዱ ስራዎች መካከል ሌላኛው ነው፡፡ በሚሰሩ ስራዎች ላይ በመመካከር የተዘጋጀው የድርጊት መርሀግብሩን ተከልሶ እንዲጸድቅ ይደረጋል፡፡
ስራውን መጀመር
ለእውቅና አሰጣጡ ከሚያስፈልጉት ጉዳዮች መካከል ከስፖርት ወዳድ ማህበረሰብ፣ ከአድናቂዎቹና በመርሀግብሩ ላይ እንዲሳተፉ ከተለዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች የሚሰበሰበው ገንዘብ አንዱ ነው፡፡ ይህንን ገንዘብ በተሻለና ተአማኒነት ባለው መልኩ ለማሰባሰብ እንዲቻል በባለቤቱ በመሸሻ ወልዴ ስም ዝግ የባንክ አካውንት/አካውንቶች መክፈቱ አስፈላጊ በመሆኑ የባንክ አካውንቱ/አካውንቶቹ እንዲከፈት/ቱ ይደረጋል፡፡ በስሙ የተከፈተውን የባንክ አካውንት ለህብረተሰቡ የማሳወቅና የገንዘብ ማስገባቱ የሚጠናቀቅበትን ጊዜ ማሳወቅ፤ በእውቅና ስርዐቱ ላይ እንዲሳተፉ የተለዩ ግለሰቦችን በቡድን በመሆን የማነጋገርና በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ገንዘቡ ገቢ እንዲሆን የመከታተልና የማስተባበር ስራ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በውጭ ሀገራት አላማውን የሚደግፉ የቀድሞ ተጫዋቾች፣ ደጋፊዎችና ሌሎችም እንዲሳተፉ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በአውሮፓ እና በደቡብ አፍሪካ ያሉ በመርሀግብሩ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እንዲካሄድ ይደረጋል፡፡
በጋዜጠኛው ስም የተከፈቱ አካውንቶች
United Bank. (1140411652300018)
Awash bank (01320499727900/8350)
CBE. (1000414344732)
Oromia. (1000800011845)
Wegagen (0886934530101)
Abyssinia. (57534378)
Dashin. (5026018283)
ለመሸሻ ወልዴ እውቅና ለመስጠት እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ያበረከተውን አስተዋጽኦና የሰራውን ስራ መሰረት በማድረግ በመሆኑ ይህንን በተመለከተ የመሸሻ ወልዴን አጠቃላይ የህይወት ታሪክና በስፖርት ያሳለፋቸውን አመታትና የሰራቸውን ስራዎች የሚያሳይ ለታሪክ መቀመጥ የሚችል ዘጋቢ ፊልም ከተለያዩ አካላት ጋር በመመካከር እንዲሰራ ይደረጋል፡፡
የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ስራዎች
የተሰበሰበውን የገንዘብ መጠን ማወቅ፣ የተለየ ድጋፍ ያደረጉ አካላትን በመለየት የእውቅና ሰርቲፍኬት ማዘጋጀት፣ ለመሸሻ ወልዴ ስጦታ የሚሆን ነገር ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡
የእውቅና አሰጣጥ ስነ ስርዐቱ በጳጉሜ ወር 2013 ዓ.ም በተመረጠ ቦታ ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት እንዲከናወን የሚደረግ ሲሆን በእለቱ የተዘጋጀው ዘጋ ፊልም እንዲታይ ይደረጋል፡፡
ከመሸሻ ወልዴ ጋር በመተባበር በተገኘው ገንዘብ ዘለቄታዊ ጥቅም ያለውና መሸሻንና ቤተሰቡን ሊጠቅም የሚችል ሁኔታ የሚፈጠርበትን/ስራ የሚሰራበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣
የእውቅና አሰጣጥ ስራው የሚከናወንበት ጊዜ
የእውቅና አሰጣጥ ስነስርዐቱ ከሰኔ ወር 2013 ሁለተኛ ሳምንት ጀምሮ እስከ ነሐሴ ወር 2013 መጨረሻ ሳምንት ድረስ የሚከናወን ሲሆን የመዝጊያ መርሀግብሩ በጳጉሜ ወር 2013 ከምሽቱ 12፡00 ሰዐት ጀምሮ በተመረጠ ቦታ/ ሆቴል የእራት ግብዣ ስነስርዐት ተዘጋጅቶ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እንዲካሄድ እቅድ ተይዟል፡፡
የድርጊት መርሀግብሩ ከዚህ እንደሚከተለው ተቀምጧል፡-