የዓለም አቀፉ የእግርኳስ የበላይ አካል ፊፋ ወርሀዊ የብሔራዊ ቡድኖች የደረጃ ሰንጠረዥን ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርጓል።
በዚህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባለፈው ወር ከነበረበት 145ኛ ደረጃ ሶስት ደረጃዎችን በመቀነስ 148ኛ ላይ ተቀምጧል። ይህም በ2012 ዓመተ ምህረት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረበት የ151ኛ ደረጃ በኋላ ዝቅተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።
ቡድኑ ከአፍሪካ አስቀድሞ በነበረበት የ43ኛ ደረጃ ቀጥሏል።
ባለፈው ወር 1063 ነጥቦች ተሰጥቶት የነበረው ቡድኑ በዚህ ወር ግን ወደ 1049.28 ዝቅ ብሏል።
- ማሰታውቂያ -
በዚህ ወር ከጊኒ ብሔራዊ ቡድን ጋር ባደረጋቸው ሁለት የ2025 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች 3 – 0 እና 4 – 1 መሸነፉ የሚታወስ ነው።