የብሔራዊ ቡድናችን ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በጥር ወር ለሚካሄደው ውድድር ቅድመ ዝግጅት እንዲረዳ እና ተጫዋቾች በየክለባቸው በውድድር ላይ እያሉ ተገቢውን ክትትል እና ዝግጅት ለማከናወን እንዲረዳ እጩ የተጨዋቾች ዝርዝር ማቅረብ አስፈላጊ በመሆኑ ለ42 ተጫዋቾች ጥሪ ማቅረባቸውን የገለፁ ሲሆን በቀጣይ የ28 ተጨዋቾችን ዝርዝር እንደሚያሳውቁ እና እጩ ተጫዋቾችም የዝግጅት ጊዜው እስኪጀምር ድረስ አቋማቸውን በመጠበቅ ውድድራቸውን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር እስከ ታህሳስ 17 እየተካሄደ እንደሚቀጥል የተገለፀ ሲሆን ከታህሳስ 18 ጀምሮ ብሑራዊ ቡድኑ ለቻን ውድድር ቅድመ ዝግጅቱን የሚጀምር ይሆናል።

ጥሪ የተደረገላቸው 42 ተጫዋቾች ዝርዝር ይህንን ይመስላል፦

ግብ ጠባቂዎች
ፋሲል ገ/ሚካኤል ባህር ዳር ከተማ
በረከት አማረ ኢትዮጵያ ቡና
ዳግም ተፈራ መቻል
ባህሩ ነጋሽ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዳንኤል ተሾመ ድሬዳዋ ከተማ
ተከላካዮች
አስራት ቱንጆ ኢትዮጵያ ቡና
ሱሌማን ሀሚድ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ረመዳን የሱፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሄኖክ አዱኛ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዓለምብርሃን ይግዛው ፋሲል ከነማ
ጊት ጋትኩት ሲዳማ ቡና
አስቻለው ታመነ ፋሲል ከነማ
ምኞት ደበበ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ብርሃኑ በቀለ ሃዲያ ሆሳዕና
ያሬድ ባየ ባህር ዳር ከተማ
ፍሬዘር ካሣ ሃዲያ ሆሳዕና
ፈቱዲን ጀማል ባህር ዳር ከተማ
ገዛኸኝ ደሳለኝ ኢትዮጵያ ቡና
አማካዮች
አማኑኤል ዮሐንስ ኢትዮጵያ ቡና
ጋቶች ፓኖም ቅዱስ ጊዮርጊስ
ይሁን እንዳሻው ፋሲል ከነማ
ከነዓን መርክነህ መቻል
መስኡድ መሐመድ አዳማ ከተማ
በዛብህ መለዮ ፋሲል ከነማ
ናትናኤል ሰለሞን ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ቢኒያም በላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፍሬው ሰለሞን ሲዳማ ቡና
ታፈሰ ሰለሞን ፋሲል ከነማ
ፉአድ ፈረጃ ባህር ዳር ከተማ
አጥቂዎች
በረከት ደስታ መቻል
ቸርነት ጉግሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ይገዙ ቦጋለ ሲዳማ ቡና
አማኑኤል ገ/ሚካኤል ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዳዋ ሆቴሳ አዳማ ከተማ
ብሩክ በየነ ኢትዮጵያ ቡና
ኪቲካ ጀማ ኢት. መድን ድርጅት
ዱሬሳ ሹቢሳ ባህር ዳር ከተማ
ቢኒያም ጌታቸው ድሬዳዋ ከተማ
ጌታነህ ከበደ ወልቂጤ ከተማ
ሽመክት ጉግሳ ፋሲል ከነማ
ምንይሉ ወንድሙ መቻል
ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ፋሲል ከነማ