ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
መንግስት ለእግርኳስ ትኩረት እንደሚሰጥ አረጋገጡ
“ለእግርኳሳችን ለተሰጠው ትኩረትና ክብር
እናመሰግናለን”
አቶ ደረጄ አረጋ
/የአ/አ እግርኳስ ፌዴ ፕሬዝዳንት/
የመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ እግርኳሳዊ ዕድገትን ለማጠናከርና ከተማዋ ላይ ያለውን የሜዳ ዕጥረት ለማስወገድ የሚቻለውን እንደሚያደርጉ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።
ፕሪሞ ሜዳ ላይ ባርኔሮና ልደታ ክፍለ ከተማ ባደረጉት የወዳጅነት ጨዋታ በልደታ ክፍለ ከተማ 2ለ0 አሸናፊነት የተጠናቀቀውን ጨዋታ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቦታው ተገኝተው መከታተላቸው ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክለቦቹም ጋር የተወያዩ ሲሆን ለቀረበላቸው ጥያቄም በሰጡት ምላሽ መንግስት እግርኳሱን ለማበረታታት ቆርጦ መነሳቱን ገልጸው የከተማዋን እግርኳሳዊ ዕድገትን ለማጠናከርና ያለውን የሜዳ ዕጥረት ለማስወገድ ድጋፉን እንደሚያደርግ አረጋግጠውላቸዋል።
- ማሰታውቂያ -
የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ደረጄ አረጋ በበኩላቸው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ መገኘት መደሰታቸውን ገልጸው ” ለእግርኳሳችን ለተሰጠው ትኩረትና ክብር እናመሰግናለን። እኛም እግርኳሱን ለመምራት የተሰጠንን ሃላፊነት በመወጣት ዕውቀታችን ለእግርኳሳችን በሚለው መርሃችን መሰረት የሚቻለንን ሁሉ እናደርጋለን” ሲሉ ቃል ገብተዋል።
የባርኔሮ ዋና አሰልጣኝ ጸጋ ማሞ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፕሪሞ ሜዳ ተገኝተው በሰጡት ማበረታታትና እግርኳሱ አንዱ የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን በመግለጻቸው አመስግኖ ፌዴሬሽኑ የከተማውን እግርኳስ ከማነቃቃት አንጻር ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ እየሰራ ያለውን ስኬታማ ስራ አወድሷል።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከቀናት በፊት 15 ሜዳን” በአካል ተገኝተው ማስመረቃቸው ይታወሳል።