ሰበታ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ቅሬታዎች በዝተውበታል በዚህ ሳምንት የመሐል ተከላካዩ በረከት ሳሙኤል የልቀቁኝ ደብዳቤ ያስገባ ሲሆን አሁን ደግሞ ዱሬሳ ሹቢሳ ቅሬታውን ለፌዴሬሽኑ አስገብቷል።
ዱሬሳ ሹቢሳ የ2013 ዓ.ም የሁለት ወር ደሞዝና ጥቅማጥቅም እንዲሁም የ2014 ዓ.ም የሁለት ወር ደሞዝ እና ጥቅማጥቅም በአጠቃላይ የአራት ወር ደሞዝ እና ጥቅማጥቅም እንዲከፈለው ለፌዴሬሽኑ ቅሬታውን አስገብቷል ።
ተጫዋቹም ክለቡ በሰባት ቀናት ውስጥ ምላሽ ካልሰጠው መልቀቂያውን ከፌዴሬሽኑ እንደሚወስድም ጭምር ገልጿዋል።