በክረምቱ የተጫዋቾች የዝዉዉር መስኮት ሰበታ ከተማን ተቀላቅሎ የነበረዉ ናሚቢያዊዉ አጥቂ ጁንያስ ናንጄቦ ከክለቡ ጋር በስምምነት መለያየቱ ተሰምቷል።
ከዚህ ቀደም ለወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እና ድሬዳዋ ከተማ መጫዎት የቻለዉ አጥቂዉ ለሰበታ ከተማ ለመጫወት ፊርማዉን ካኖረ ከአራት ወራት ቆይታ በኋላ ከክለቡ ጋር በስምምነት መለያየቱ ዕርግጥ ሆኖአል።
ለመለያየታቸዉ እንደምክንያት የተጠቀሰዉም ተጫዋቹ ክለቡን ከተቀላቀለበት ጊዜ አንስቶ እስከ ሰባተኛዉ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በነበሩት ጨዋታዎች ላይ የነበረዉ ዕንቅስቃሴ እንደታሰበዉ መሆን አለመቻሉን የገለፁት የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ ምንም እንኳን እኛ በአቋሙ ደስተኞች ባንሆንም ተጫዋቹ በራሱ ፍቃድ መልቀቂያ በማስገባቱ ምክንያት በስምምነት ለመለያየት መወሰናቸዉን ለሀትሪክ ስፖርት ድህረ-ገጽ ገልፀዋል ።
ተጫዋቹ በዛሬው ዕለትም ከሀዋሳ ወደ አዲስአበባ በማምራት ከክለቡ ሀላፊዎች ጋር በመገናኘት በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ፅህፈት ቤት በመገኘት በስምምነት ዉላቸዉን እንደሚያፈርሱ ታዉቋል።