አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው /ሞሪንሆ/ ሰበታ ከተማን ለ3 አመት ለማሰልጠን ተስማምቷል።
ውጤታማና ጠንካራ ቡድን በመገንባት የሚታወቀው ዘላለም ዛሬ ጠዋት ከክለቡ አመራሮች ጋር ድርድር ካደረገ በኋላ እስከ 2016 ድረስ ሰበታን ለማሰልጠን ተስማምቷል።
በወላይታ ድቻ አሰልጣኝነት ክለቡ ያለውን ድክመት አርሞ ጠንካራ ቡድን የፈጠረ ሲሆን በዲሲፕሊን ላይ ባለው አቋምና የጨዋታ ዘመን ሳይኖረው ውጤታማ መሆኑ ሞውሪንሆ የሚል ቅጽል አሰጥቶታል።
ሰበታ ከተማ አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱን እንደማያገኝ ከተረጋገጠ በኋላ ከበርካታ አሰልጣኞች ጋር ስሙ ቢነሳም በመጨረሻ ሀላፊነቱን ለአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ሰጥቷል።