ባለፉት አመታት ለተለያዩ የሊጉ ክለቦች መጫወት የቻለዉ የግብ ዘቡ አቤል ማሞ ለአዲስ አዳጊዉ ክለብ ሻሸመኔ ከተማ ለመጫወት ፊርማዉን ማኖሩ ታውቋል።
ከዚህ ቀደም ለሙገር ሲሚንቶ ፣ መከላከያ ፣ ኢትዮጵያ ቡና መጫወት የቻለዉ እንዲሁም ያለፈዉን አንድ አመት ደግሞ በአዞዎቹ ቤት አርባምንጭ ከተማ ቆይታ የነበረዉ ግብ ጠባቂዉ አቤል ማሞ አሁን ደግሞ ለአዲስ አዳጊዉ ክለብ ሻሸመኔ ከተማ ለመጫወት ፊርማውን ማኖሩ ታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪም አዲስ አዳጊዉ ክለብ የነባር ተጫዋቾቹን ወጋየሁ ብርቄ ፣ አሸናፊ ጥላሁን እና ጌታለም ማሙየ ውል ለተጨማሪ አመታት ማራዘሙም ይፋ ተደርጓል።