ዋልያዎቹ ታሪካዊ የመሀል ሜዳ ተጫዋች ሽመልስ በቀለ ጥሩ የሚባል የውድድር ዓመትን ካሳለፈበት ክለቡ ጋር በስምምነት በመለያየት ወደ አዲስ ክለብ ማምራቱ ተረጋግጧል።
ከዚህ ቀደም በግብፅ ሊግ ለፔትሮጀት እና ምስር አል መቃሳ ተጫዉቶ ማሳለፍ የቻለዉ አማካዩ ሽመልስ በቀለ ቀጣዮቹን ሁለት ዓመታት ለሌላኛዉ የግብፅ ክለብ ኢል ጉና ለመጫወት መስማማቱ ተረጋግጧል።
በተጨማሪም ” ኢትዮጵያዊዉ ታሪካዊ ተጫዋች ሽመልስ በቀለ ወደ ክለባችን መቀላቀሉን ስናበስር ኩራት ይሰማናል ” በማለት ኤል ጉና ክለብ የሽመልስ በቀለ ለክለቡ መፈረሙን አብስረዋል።