ሲዳማ ቡና የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ የቀድሞ ወጌሻውን ወደስራው እንዲመልስና ውዝፍ ደመወዙን እንዲከፍል የሰጠውን ውሳኔ እንደማይቀበል ገለጸ።
ክለቡ ህዳር 21/2014 ባወጣው ደብዳቤ ለዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ በሰጠው ምላሽም ይግባኝ እንደሚልና ያለውን ማስረጃ እንደሚያቀርብ አስታውቋል።
ዲሲፕሊን ኮሚቴው በሰጠው ብያኔ ሲዳማ ቡና ወጌሻውን ወደስራ እንዲመልስ ያለውን ውዝፍ የአምስት ወር ደመወዝ በአንድ ላይ አድርጎ በሰባት ቀን እንዲከፍል አዝዞ ይህ የማይሆን ከሆነ ከፕሪሚየር ሊጉ እንደሚታገዱና ከፌዴሬሽኑ ምንም አይነት ግልጋሎት እንደማያገኙ አስጠንቅቋል።
ሲዳማ ቡና የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ ከተቀበለ 7ኛ ቀን የሚሞላው የፊታችን ማክሰኞ ሲሆን እስከዚያው ይግባኝ መጠየቅ እንደሚችል ታውቋል። ባለው መረጃ እስከ ማክሰኞ ድረስ ይግባኙ ካልቀረበ ተቀባይነት እንደማይኖረው ታውቋል።