ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብን ላለፉት አንድ ዓመት ተረክቦ ሲያሰለጥን የሰነበተዉ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ እና ሲዳማ ቡና ተለያይተዋል።
ከሳምንት በፊት አሰልጣኙ እና ምክትላቸው ለክለቡ ሪፖርት ባለማቅረባቸዉ ከስራ ገበታቸዉ ታግደዉ የነበረ ሲሆን በዛሬው እለት ዋና አሰልጣኙ ስዩም ከበደ እና ምክትላቸዉ ቾንቤ ገብረህይወት ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይተዋል።
ሲዳማ ቡና በዘንድሮዉ የዉድድር ዓመት እስካሁን ካደረጋቸዉ 5 ጨዋታዎች 4 ነጥብ ብቻ በመሰብሰብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።