በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ እየተመሩ ለ2016 ዓ.ም የዉድድር ዘመን ወደ ስብስባቸዉ አዳዲስ ተጫዋቾችን እየቀላቀሉ እንዲሁም የነባር ተጫዋቾችን ዉል እያደሱ የሚገኙት አሊቶዎቹ ለ2016 ዓ.ም የዉድድር ዘመን ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታዉቋል።
ቡናማዎቹ ነሀሴ 9 በሀዋሳ ከተማ በሚያርፉበት ታደሰ ኢንጆሪ ሆቴል የሚሰባሰቡ ሲሆን በማግስቱ ነሀሴ 10 ጀምሮ ዝግጅታቸዉን የሚጀምሩ ይሆናል።
ሲዳማ ቡናዎች አሁን ካላቸዉ ስብስብ በተጨማሪ በቅርቡ አዳዲስ የሀገር ዉስጥ እና የዉጪ ሀገር ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸዉ እንደሚቀላቀሉ ለማወቅ ችለናል።