በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራዉ እየተመራ ለቀጣዩ የውድድር አመት ተጠናክሮ ለመቅረብ በዝውውር መስኮቱ ላይ በንቃት እየተሳተፈ የሚገኘዉ ሲዳማ ቡና እስከ አሁን ድረስ ሳሙኤል ሳሊሶ ፣ አበባየሁ ሀጂሶ ፣ ፍራኦል መንግስቱን ማስፈረማቸዉ የሚታወስ ሲሆን ደግሞ የሁለት ወሳኝ ተጫዋቾችን ዝውውር ፈፅሟል።
አንደኛዉ ፈራሚ የቀድሞዉ ዳሽን ቢራ ፣ ፋሲል ከነማ እና ላለፉት ሁለት የውድድር አመታት ደግሞ በባህርዳር ከተማ ቤት ማሳለፍ የቻለዉ ተከላካዩ ያሬድ ባየህ ሲሆን ፤ በሁለተኝነት ደግሞ ክለቡን የተቀላቀለዉ ያለፉትን አመታት በኢትዮጵያ ቡና ቤት ማሳለፍ የቻለዉ አማካዩ ሬድዋን ናስር ሆኗል። ሁለቱም ተጫዋቾች የሁለት አመት ኮንትራት በሲዳማ ቡና ቤት መፈረማቸው ታውቋል።