የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን በበርካታ ጨዋታዎች ላይ በአጥቂ መስመር ላይ ወክሎ መጫወት የቻለው እና በክለብ ደረጃ ለረጅም አመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የተመለከትነው ሳልሀዲን ሰይድ ለወራት ክለብ አልባ ሆኖ ከቆየ በኋላ በአሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ ወደሚመራው ሲዳማ ቡና ማምራቱ ተሰምቷል ።
ተጫዋቹ ከፈረሰኞቹ ጋር ከተለያየ በኋላ ወደ ጅማ አባጅፋር ለመዘዋወር ከጫፍ ደርሶ የነበረ ቢሆንም በመጨረሻ ሰዓት ላይ ዝውውር ሳይሳካ መቅረቱ የሚታወስ ነው ።
ሲዳማ ቡና በዚህ የዝውውር መስኮት ላይ ከተለያዩ የአጥቂ መስመር ተጫዋቾች ጋር ስሙ ሲያያዝ የቆየ ሲሆን በስተመጨረሻ ግን ሳልሀዲን ሰይድን ወደ ቡድኑ መቀላቀል ችሏል ።
ሲዳማ ቡና የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታውን የፊታችን ሀሙስ ከቀኑ በ9:00 ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የሚያደርግ ይሆናል ።