ከቀናት በፊት አሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመን ዋና አሰልጣኝ አድርገዉ የሾሙት ሲዳማ ቡናዎች አሁን ደግሞ በይፋ ወደ ዝውውር ገበያዉ በመግባት ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርመዋል።
የመጀመሪያዉ ፈራሚ ከዚህ ቀደም ለአርሲ ነገሌ እና ገላን ከተማ እንዲሁም የዉድድር አመቱን በአዲስአበባ ከተማ ማሳለፍ የቻለዉ አማካዪ ሙሉቀን አዲሱ ሁለት አመት በሚቆይ የስምምነት ዉል ወደ ሲዳማ ቡና ማምራቱ ተረጋግጧል።
ሌላኛዉ ፈራሚ ደግሞ ከዚህ ቀደም ለመቀሌ 70 እንደርታ ፣ ድሬዳዋ ከተማ ፣ ሲዳማ ቡና እና አርባምንጭ ከተማ መጫዎት የቻለዉ የመስመር አጥቂዉ እንዳለ ከበደ ሲሆን ተጫዋቹ ለሁለት አመታት በሚቆይ ዉል ወደ ቀድሞ ክለቡ ማምራቱ ተረጋግጧል።