በአሰልጣኝ ወንድማገኝ ሀይሉ እየተመሩ በዝዉዉር ገበያዉ ላይ በንቃት በመሳተፍ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ በመቀላቀል ላይ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች ተጨማሪ ተጫዋች ከኢትዮጵያ ቡና ማስፈረማቸዉ ተረጋግጧል።
ከዚህ ቀደም ለመከላከያ መጫወት የቻለዉ እና ያለፉት ሶስት አመታት በኢትዮጵያ ቡና ቤት ቆይታ የነበረዉ ዊሊያም ሰለሞን በዛሬዉ ዕለት ቀጣዩቹን ሁለት አመታት ለሲዳማ ቡና ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።