ያለፉትን ዓመታት በ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን የቻሉት ሲዳማ ቡናማዎች ከአሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ ጋር መለያየታቸው የሚታወስ ነው ።
ከ ክለቡ እየወጡ ባሉ መረጃዎች ሲዳማ ቡናዎች ቀሪውን የውድድር ዘመን ቡድናቸውን እንዲያሰልጥን አንጋፋውን አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሀይሌ መቅጠራቸው ተሰምቷል ።
አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሀይሌ ያለፉትን ሁለት አመታት ከ ጅማ አባ ጅፋር እና መቐለ 70 እንደርታ ጋር በተከታታይ የሊጉን ዋንጫን ሲያሳኩ በትራን ኢትዮጵያ ፣ ኢትዮጵያ መድህን ፣ መከላከያ ፣ ደደቢት ፣ ጅማ አባ ቡና ጨምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማሰልጠናቸው የሚታወስ ነው ።