በዘንድሮው የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ደካማ ጉዞን እያደረጉ ከሚገኙ ክለቦች አንዱ የሆነው ሲዳማ ቡና ዛሬ ረፋድ ላይ የ ክለቡ ቦርድ አመራሮች ከ ሲዳማ ቡና ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋር መነጋገራቸው ተሰምቷል ።
በስብስባቸው የ ክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ ሳሳሞ እንዲሁም የ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ እና ምክትላቸው ያሬድ ገመቹ ጋር መለያየታቸውን ያገኘነው መረጃ ያሳያል ።
ሀትሪክ ስፖርት ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመገናኘት ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል ።