ከግማሽ ቢሊዮን በላይ ተከታዮችን በዓለም ላይ ማፍራት የቻለው ቲክ ቶክ የተሰኘው የቻይናው የማሕበራዊ ትስስር ገፅ በበርካታ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ተጠቃሚዎችን ማፍራት ችሏል ።
በዚህ ቲክቶክ በተሰኘው መተግበሪያ የበጎ አድራጎት ስራዎችን እየሰራ በሚሊዮኖች ዘንድ እይታን ያተረፈው የባህርዳሩ ግብ ጠባቂ ስነጊዮርጊስ እሸቱ የዛሬው የሀትሪክ ስፖርት እንግዳ ነው ተከታተሉን።
የባህርዳር ከተማው ግብ ጠባቂ ስነጊዮርጊስ እሸቱ ስለ ባህርዳር ቆይታው ፣ ስለ ሊጉ እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን ከሀትሪክ ስፖርቱ ድህረገጽ ፀሀፊ ቅዱስ ዮፍታሔ ጋር ቆይታን አድርጓል ተከታተሉት ።
በዘንድሮው የውድድር ዓመት ክለቦች ፊታቸውን ወደ ሀገር በቀል ግብ ጠባቂዎች ማዞር መጀመራቸው መልካም ጅምር ነው ። በአብዛኛው የሀገር ውስጥ በረኞች እድሎችን ሳናገኝ ብንቆይም አሁን ለእኔም ባይሆን ለጎደኞቼ ወይም የ ሙያ አጋሮቼ እድል በመሰጠቱ እራሳቸውን እያሳዩ ይገኛሉ ። በዚህም ደስተኛ ነኝ እኔም እድሉን ለማግኝት ያቅሜን ሁሉ እያደረኩ ነው።
- ማሰታውቂያ -
የጣና ሞገዶቹ ያለፉትን ጨዋታዎች በሀገር ውስጥ ግብ ጠባቂዎች መጫወታቸውን እና የጨዋታን ጊዜ በተመለከተ ስነጊዮርጊስ የሚከተለውን ሀሳብ አስፍሯል ።
” በእነዚህ ነገሮች ውሳኔ መስጠት የእኔ ሀላፊነት አይደለም ፣ በእርግጥ የአሰልጣኜንም ፋሲል ተካልኝ ውሳኔም አከብራለሁ ። እኔ እንደ አንድ ተጫዋች ልምምዶችንም ሆነ የግል ስራዎችን በርትቼ እየሰራሁ ነው ። አምላክ ሲፈቅድ እድሉ ይመጣል ብዬ አምናለው ፣ ያኔ እራሴን ለማሳየት እሞክራለሁ ።
የ ዲኤስቲቪ መምጣት እኔ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ነው እማየው የሀገራችንም ስፖርት ወደ አንድ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል ብየ አስባለሁ ። ለእኛ ለተጫዋቾችም ስህተቶቻችንን እንድናርም እየረዳን ሲገኝ ለአሰልጣኞችም በተወሰነ መልኩ ያግዛቸዋል ብየ አስባለሁ ።
ምክንያቱም ከጨዋታ በኋላ የምናገኛቸው የጨዋታ ቪድዮዎች ስህተቶቻችንን እንድናስተካክል እድል እየሰጡን ይገኛሉ ። ከፍ ሲልም ለውጭው ገበያ እራስን ለማሳየት በር የከፈተ ነው ።
ስነጊዮርጊስ እሸቱ ከ እግር ኳሱ በዘለለ አሁን ላይ በማህበራዊ ትስስር ገፆች በሚሰራቸው የበጎ አድራጎት ስራዎቹ ሰለመታወቁ?
” እውነት ለመናገር እኛ ኢትዮጵያውያን መስጠት ባህላችን አድርገነዋል ፣ እኔ ዛሬ መጥቼ አስተምራለሁ ብዬ ሳይሆን አሁን የመጣብን ፖለቲካው ያመጣው ጣጣ እንዳንተሳሳብ አድርጎናል ።
ምን አልባት ማስታወስ ከቻልኩ ብዬ እንጂ በእርግጥ እግዚአብሔር ፈቅዶ ሰዎችም ጋር በደምብ እየደረሰ ነው ። አሁን በውጭውም የሚኖሩ ሀገር ውስም ያሉ እህት ወንድሞች ለወገኔ እያሉ እንዳደርስ ይልኩልኛል ።
https://vm.tiktok.com/ZMedeSofp/
እኔም እያደረስኩ ነው የተወሰኑ እህት ወንድሞችን እየረዳን ነው እንደ አንድ ዜጋ ለሀገሬ የሆነ ነገር አድርጌ ማለፍ እፈልጋለሁ ፣ እየሞከርኩም ነው አምላክ ይጨመርበት። ”
ስነ ጊዮርጊስ እሸቱ ስለ ባህርዳር ከተማ ?
” ቡድናችን በሊጉ ጥሩ ተጫዋቾችን ከያዙ ከለቦች አንዱ የኛ ባህርዳር ከነማ ነው ። ቡድኑ ውስጥ መተሳሰብ ጥሩ የቡድን መንፈስ አለ ። አሰልጣኛችንም ፋሲል ተካልኝ ለእኔ በሊጉ ውስጥ ጥሩ አሰልጣኞች ከምላቸው ውስጥ አንዱ ነው ። አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ወጣት ነው የጥሩ ስብህናም ባለቤት ነው።
በቀጣይ ዙር የሊጉ ጨዋታዎች በ ባህር ዳር ቆይታችን ጥሩ ይሆናል ብየ አስባለሁ ። እምናቀው ሜዳ ነው በዛ ላይ ምቹ ነው ያቅማችንን ካደረግን ውጤቱ ጥሩ እማይሆንበት ነገር የለም ።
በሊጉ ያለው የቡድኖች ነጥብ በጣም ተቀራራቢ ነው ማን ሻምፒዮን እንደሚሆን እንደቀደሙት መገመት ከባድ ይመስለኛል ፣ እኔ እንደ መልካም አጋጣሚ አየዋለው ።
በቀጣዩ ዙር በከተማችን ብንጫወትም ደጋፊው መግባት አይችልም ፣ ቢሆንም ከዚህ በፊት እንደሚያደርጉት ድጋፍቸው አይለየን ለደጋፊው ክብር አለኝ በደጋፊው ብዙ አልፈናል።”
በቀጣይ ምን ያስባል ?
የቀጣዩ ጊዜ እሚወሰነው በዚህ የውድድር አመት በምታሳያው አቅም ነው ። እንዳልኩህ በርትቼ እየሰራሁ ነው አምላክ ይጨመርበት ።