የተመሰረተበት ዓላማ ከስያሜው አንስቶ ጥሩ መልዕክት አለው። ስፖርት ለሰላም, ለወንድማማችነት, ለጋራ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ሳይታለም የተፈታ እውነታ ነው። የረጅም ዘመን የስታዲየም ታዳሚ በመሆናቸዉ ወደ ኃላ ተመልሰዉ የአገራቸዉ ሊግ ላይ ይንፀባረቁ የነበሩትን ኢ-ስፖርታዊ ድርጊቶች የስታዲየም ታዳሚን ብቻ ሳይሆን ስለ እግር ኳስ ምንም ስሜቱ የሌለው እንኳን አሳዛኝ ነገሮች የሚፈፀሙበት ቦታ በመሆኑ ይኽም ከእለት እለት ስፖርታዊ ውድድሮች በተለይ እግር ኳስ ላይ የታዩ ፍፁም ከስፖርቱ ጋር አብረው መጓዝ የሌለባቸው ነገሮች በምንም ዓይነት መልኩ ማስቀረት ባይችሉ እንኳን እንዲቀር መስመር መጀመር አለብን ብለዉ ከኢትዮጵያ ቡና እና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጋር በጋራ በመሆን መወያየት ጀመሩ።
ይኽም የሆነበት ምክንያት ቅድሚያ እዚሁ ከተማቸዉ ላይ ያሉትን ሁለቱ የበርካታ ደጋፊ ባለቤቶች ለለውጡ ማድረግ ያለባቸዉን ነገር መነጋገር ጀመሩ። በዚህ ሂደትም በሞራል በሃሳብ ‘ይኽንን ብታደርጉ ጥሩ ነው’ በማለት እንደ አንድ ዜጋ የቀድሞ የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዮናስ አረጋዊ ለረዷቸዉ እርዳታ የሚያመሰግኑት አባላቱ። እንዲህ እንዲህ እያለ በተወሰኑ ሰዎች ሃሳብ አዋጭነት እየጎለበትም እያደገም ሄደ።
ከዚህ በተጨማሪ ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን የጎዳና ላይ ማስ ስፖርት በመሳተፍ ንቁ እና ጤናማ ዜጋ ለማፍራት በሚደረገው ተሳትፎ ላይ በየጊዜው በመገኘት መነቃቃትን መፍጠር ቻሉ። ይኽንን አጋጣሚ በመጠቀም በዓይነቱ ልዩ የሆነ ‘ሸገር ደርቢ በመስቀል አደባባይ’ የሚል መሪ ቃል ያለውን እና በአህጉራችን አፍሪካ በቀዳሚነቱ ሪከርድ የያዘውን ታላቅ ማስ ስፖርት ያለምንም እንከን ደረጃውን እና ጥራቱን እንዲጠብቅ አድርገው በሁለቱ ደጋፊዎች መሃከል የነበረውን ክፍተት በማቀራረብ መስራት ቻሉ።
- ማሰታውቂያ -
በዚህ ፕሮግራም ባህላዊ የስፖርት ውድድር ወቅቱ የገና ሰሞን ስለነበር እንደ ገና ጨዋታ በማከናወን እንዲሁም ፉትሳል በሁለቱ ክለቦች ደጋፊዎች መሃከል ማካሄድም ችለዉ ነበር። በቁጥር 5000 (አምስት ሺህ) የሚሆኑ አርማዎች ተሰርተው ለደጋፊዎችም ተሰጥተዋል። ትውልድ ላይ የማቀራረብ ስራን ሰርተዉም ተሳክቶላቸዋል።
የስፖርት ለሰላም ዓላማ በሁለቱ የመዲናዋ ትልልቅ ክለቦች መሃከል ለዘመናት የነበረውን ከስፖርት ውጭ የሆነውን ጉዳይ መፍታት የነበረ ሲሆን። ይኽንንም በመስቀል አደባባይ በሰሩት ስራ ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም አምጥተው ይበልጥ እንዲጎለብት ማድረግ አለብን በሚል በሸገር ካፕ በቀድሞ ስሙ ‘ሲቲ ካፕ’ ላይ በማሳየት ጥሩ መልዕክት ማስተላለፍ ቻሉ።
ከዚህም በኃላ አዲስ አበባ ላይ በነበረው የመቀለ 70 እንደርታ እና የፋሲል ከነማ የአሸናፊዎች አሸናፊ የዋንጫ ጨዋታ ሰላማዊ በሆነ መልኩ በመጠናቀቁ በክልል ክለቦች መሐከል የነበረው በእግርኳስ ምክንያት ይከሰቱ የነበሩ የስፖርታዊ ጨዋነት ችግሮች መወገዳቸው በገሃድ ተስተዋለ። ‘ስፖርት ለሰላም’ መስራት ከሚገባው በላይ ስራውን ደፍሮ ሰርቶ የቆመ ማህበር ሁልጊዜም አዲስ ነን ብሎ አይዘናጋም የሚሉት አባላቱ። በየጊዜው አዲስ እና ጠንካራ ሃሳቦችን እያመጡ ጉዟቸዉን ቀጠሉ።
በአዲስ አበባ የተጀመረው ‘ስፖርት ለሰላም’ ወደ ክልል መውጣት አለበት ብለዉ በማሰብ አዲስ ሃሳብ አመጡ። ይኽም የዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት ተደርጎለት በየተራው ሊሰራ የታሰበው ፕሮግራም በወቅቱ በነበሩት የሰላም ሁኔታ አለመረጋጋት ቢቋረጥም በዚያ ውስጥ ሆኖ አምቦ እና ደብረ ብርሃን እንዲሁም ጅጅጋ እና አዋሳ በተሳካ ሁኔታ ተደርጓል።
ስፖርት ለሰላም በዚህ ብቻ ሳይገታ አንድ ሃሳብ በማምጣት ድሬዳዋ ላይ በጎርፍ የተጎዱ ወገኖቻቸውን ለምን አናግዝም የሚል ሃሳብ ይዘዉ ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመሆን እንዲሁም ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ጋር በመተባበር ጥሩ እና የተሳካ ጊዜ አሳልፈዋል። የተወሰኑ ቤቶችን ጠግነዉ ስፖርት ለሰላም በድሬ መስርተው መመለስ ቻሉ።
‘ስፖርት ለሰላም’ አገራዊ ጥሪዎች
አረንጓዴ አሻራን በመደገፍ ብቻ ሳንገቱ በተከታታይ በመሳተፍ ጉልህ ድርሻንም ተወጥተዋል። ‘ደሜን ለወገኔ’ በሚል አዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ባዘጋጀው መርሃ ግብር ላይም ተሳትፈዋል። በኮቪድ ምክንያት የእለት ጉርሳቸውን ያጡ ወገኖችንም በአዲስ አበባ ስታዲየም በመመገብ የወገን አልኝታነታቸዉን በተግባር አሳይተዋል።
ይኽ ጅማሬያቸዉ በመሆኑ ከዚህ በተሻለ መልካም ራዕይ ያለው ማህበር እንዲሆን እና በቀጣይ ጠንካራ ተሳትፎው ለትውልዱ የሚበጅ ጥሩ መልዕክት ለማስተላለፍ የተዘጋጀ ከክልል ስፖርት ቤተሰብ ጋር በጋራ በመሆን ወንድማማችነት በመፍጠር እግር ኳሱ የሰላም መድረክ እንዲሆን በፅኑ የሚመኝ ማህበር መሆኑን አባላቱ ይናገራሉ።