የሲዳማ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የመክፈቻ ስነስርዓት በዛሬው እለት በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች እና የስፖርት ቤተሰቡ በተገኙበት በኢንተርናሽናል ስታዲየም (የዉጪዉ ሜዳ) ተካሂዷል።
በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍሬዉ አሬራ ፣ የሲዳማ ክልል ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ም/ኃላፊና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደስታ ለገሰ ፣ የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ኃላፊ አቶ አክሊሉ አለሙ ፣ የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ት/ስ/ዉ/ዳ/ዳይሬክተር አቶ እንግዳ ባዴጎ ፣ የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ አንበሴ አበበ ፣ የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት አቶ ማርቆስ ኤልያስ ፣ የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ስራ አስኪያጅ አቶ አቡሽ አሰፋ እና ሌሎችም ተገኝተዋል።
የመክፈቻ ጨዋታዉን 5ኛ ካምፕ እና BFC ምስራቅ የተጫወቱ ሲሆን 5ኛ ካምፕ 3-2 በሆነ ዉጤት አሸንፏል።
ቀጣይ የምድብ ጨዋታዎች ነገ በቀን 7/9/2015 ዓ/ም ቀጥለዉ የሚካሄዱ ሲሆን ጠዋት 3:00 ሰአት አዲስ ከተማ ከ ኢትዮ ሳሙና 5:00 ሰአት ወ/ገነት ከ አለታ ወንዶ 7:00 ሰአት ሀዋሳ ተስፋ ከ ዳዬ ከተማ ጋር በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲየም (የዉጪዉ ሜዳ) ይጫወታሉ።