በዘንድሮው የዉድድር አመት እንደተጠበቁት መሆን ያልቻሉት ፈረሰኞቹ ለቀጣዩ የዉድድር አመት ተጠናክረው ለመቅረብ ይረዳቸው ዘንድ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው መቀላቀል ጀምረዋል።
በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ዘንድሮ ጎልተዉ መዉጣት ከቻሉት ተጫዋቾች መካከል የሚጠቀሱት ሁለቱ የወላይታ ዲቻ ተጫዋቾች ቸርነት ጉግሳ እና በረከት ወልዴ ቅዱስ ጊዮርጊስን በይፋ ተቀላቅለዋል።
ፈጣኑ የመስመር አጥቂ ቸርነት ጉግሳ ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር በዝዉዉር ሲያያዝ ቢቆይም በመጨረሻም ማረፊያ ቅ/ጊዮርጊስ መሆኑ ተረጋግጧል። የመስመር አጥቂዉ ለሁለት አመት በሚቆይ የውል ስምምነት ፊርማዉን አኑሯል።
ሌላኛው የወላይታ ዲቻ ተጫዋች የሆነዉ አማካኙ በረከት ወልዴ እንደ ክለብ አጋሩ ቸርነት ሁሉ በሁለት አመት የኮንትራት ስምምነት ቅዱስ ጊዮርጊስን መቀላቀል ችሏል።
- ማሰታውቂያ -
ሁለቱን ወሳኝ ተጫዋቾች ማስፈረም የቻሉት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ምንም እንኳን እስከ አሁን ድረስ ዋና አሰልጣኝ መሾም ባይችሉም፤ በሚቀጥሉት ጊዜያት ዉስጥ በዝዉዉሩ በንቃት በመሳተፍ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል።