በዘንድሮው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ 3ኛ ደረጃን ይዘዉ ማጠናቀቅ የቻሉት ፈረሰኞቹ ዋና አሠልጣኝ ከመሾማቸው በፊት በዝውውር ገበያው ላይ በንቃት ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ። እስከ አሁን ድረስም ቸርነት ጉግሳን እና በረከት ወልዴን ማስፈረማቸዉ ይታወሳል።
አሁን ደግሞ ምኞት ደበበን ከሀዋሳ ከተማ ፤ቡልቻ ሹራ ከሰበታ ከተማ ፤ሱለይማን ሀሚድን ከሀድያ ሆሳዕና ማስፈረማቸዉ ተረጋግጧል።
በአዳማ ከተማ ቤት ለአራት አመታት ያክል መጫወት የቻለዉ ተከላካዩ ባሳለፍነው የዉድድር አመት ወደ ሀዋሳ ከተማ አቅንቶ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ ከቀጣዩ የዉድድር አመት ጀምሮ ለፈረሰኞቹ ለመጫወት ተስማምቷል።
ሌላኛዉ ለክለቡ ፊርማዉን ያኖረዉ ቸጫዋች ደግሞ ወጣቱ የመስመር አጥቂ ቡልቻ ሹራ መሆኑ ታዉቋል። ከክለቡ ሰበታ ከተማ ጋር ድንቅ የዉድድር አመትን ያሳለፈዉ የመስመር ተጫዋቹ ዛሬ ረፋድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ፊርማዉን ማኖሩ ተረጋግጧል።
- ማሰታውቂያ -
በተያያዘም ግዙፋ አማካኝ ጋቶች ፓኖም ፈረሰኞቹን መቀላቀሉ ዛሬ በይፋ ተረጋግጧል። አማካኙ በዉድድር አመቱ ግማሽ ላይ ወላይታ ዲቻን ተቀላቅሎ የነበረ ሲሆን ነገር ግን ቆይታዉ ከግማሽ አመት በላይ ሊዘልቅ አልቻለም ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ቡና ቤት መጫወት የቻለዉ ጋቶች አሁን ላይ በይፋ የፈረሰኞቹ መቀላቀሉ ተረጋግጧል።
ሌላኛዉ በፈረሰኞቹን መለያ በቀጣዩ የዉድድር ዓመት የምንመለከተዉ ተጫዋች ደግሞ የመስመር ተከላካዩ ሱሌይማን ሀሚድ መሆኑ ተረጋግጧል። ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ያለውን ውል ያጠናቀቀው ሱለይማን ሀሚድ ቅዱስ ጊዮርጊስን የተቀላቀለ 6ኛዉ ተጫዋች ሆኖአል።
በተጨማሪም አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች የሳልሀዲን ባርጌቾ ፤ናትናኤል ዘለቀ፤ደስታ ደሙ፤ሀይደር ሸረፋ እና አማኑኤል ገ/ሚካኤልን ዉል ለተጨማሪ አመት ማራዘማቸዉ ተሰምቷል።