የ2014 የአንደኛውን ዙር የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 31 ነጥብ በመሰብሰብ በመሪነት ማጠናቀቅ የቻሉት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በዛሬው ዕለት የግራ መስመር ተከላካዩን ያሬድ ሀሰንን ወደ ስብስባቸዉ መቀላቀላቸው ተረጋግጧል።
ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ መድን ፣ ለሰበታ ከተማ ፣ መቀሌ 70 እንደርታ ፣ ወልደያ ከተማ ፣ ድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም ያለፉት አምስት ወራት ለአዲስአበባ ከተማ መጫወት የቻለዉ ያሬድ ሀሰን በመጨረሻም ማረፊያው ቅዱስ ጊዮርጊስ መሆኑ ዕዉን ሆኖአል።