ከአራት አመታት በኋላ የዘንድሮዉን የዉድድር አመት በሻሞፒዮንነት ማጠናቀቅ የቻሉት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በቀጣዩም አመት ይበልጥ ተጠናክረዉ ለመቅረብ ይረዳቸዉ ዘንድ በዛሬዉ ዕለት በይፋ ተጫዋች ማስፈረማቸዉ ተረጋግጧል።
ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ስሁል ሽረ እና ያለፋትን ሶስት አመታት ደግሞ በወልቂጤ ቤት በድንቅ ብቃት መጫወት የቻለዉ የግራ መስመር ተጫዋቹ ረመዳን የሱፍ በሁለት አመት በሚቆይ የኮንትራት ዉል በዛሬዉ ዕለት ወደ ረሰኞቹ ቤት ማምራቱ ተረጋግጧል።