በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ እየተመሩ የዉድድር አመቱን በድል ያጠናቀቁት ፈረሰኞቹ በቀጣዩ አመት ለሚጠብቃቸዉ አፍሪካ መድረክ እና የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ይበልጥ ተጠናክረዉ ለመቅረብ ይረዳቸዉ ዘንድ ተጫዋቾችን ማስፈረም ጀምረዋል።
በዚህም በትላንትናው ዕለት የግራ መስመር ተከላካዩን ረመዳን የሱፍን ወደ ስብስባቸዉ የቀላቀሉት ፈረሰኞቹ አሁን ደግሞ ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ስከንደርቡ ፣ ስሪያንስካ ፣ ኡመያ ፣ ሲዳማ ቡና እና መከላከያ የተጫወተውን የአማካይ ከጥቂ ስፍራ ተጫዋቹን ቢኒያም በላይን ማስፈረማቸዉ ተረጋግጧል።
በተጨማሪም ፈረሰኞቹ የፊት መስመር ተጫዋቻቸዉን አቤል ያለዉ እና የአማካዩን ያአብስራ ተስፋዬ ዉል ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸዉን ይፋ አድርገዋል።