የወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊሶች በቀጣዩም አመት በዉጤታማነት ጎዳና ላይ ለመቀጠል ይረዳቸዉ ዘንድ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ ይገኛሉ።
ከቀናት በፊት የግራ መስመር ተከላካዮን ረመዳን የሱፍን እና አማካዩን ቢኒያም በላይን ማስፈረም የቻሉት ቅዱስ ጊዮርጊሶች አሁን ደግሞ የአጥቂ አማካዩን ዳዊት ተፈራን ማስፈረማቸዉን ይፋ አድርገዋል።
ከዚህ ቀደም ለጅማ አባጅፋር መጫወት የቻለዉን እና ያለፉትን አራት አመታት ደግሞ በሲዳማ ቡና ቤት በድንቅ አቋም በመጫወት ያሳለፈዉ ዳዊት ተፈራ ለሁለት አመታት በሚቆይ ዉል ለፈረሰኞቹ መፈረሙ ተረጋግጧል።