የውድድር ዓመቱን በአዲስ አበባ ከተማ የጀመረው እና በውድድሩ አጋማሽ ላይ ወደ ፈረሰኞቹ ያቀናው የግራ መስመር ተከላካዩ ያሬድ ሀሰን ከሻምፕየኖቹ ጋር በስምምነት ተለያይቷል ።
ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም በመድህን ተስፋ እና ዋናው ቡድን ፤ በወልድያ ከተማ ፤ በመቀሌ 70 እንደርታ ፤ በድሬዳዋ ከተማ ፤ በሰበታ ከተማ እና በአዲስ አበባ ከተማ ተጫውቶ አሳልፏል ።
ያሬድ ሀሰን በ2011 ከመቀሌ ጋር የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ማሳካት የቻለ ሲሆን በዚህ የውድድር ዓመትም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ሻምፕየን መሆን በመቻሉ ሁለት ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ማሳካት የቻለ ተጫዋች መሆን ችሏል ።