በ2014 በአፍሪካ መድረክ ኢትዮዽያን የሚወክሉት ፋሲል ከነማ፣ ኢትዮዽያ ቡናና ንግድ ባንክ ይፋዊ የዝውውር መስኮት ሳይከፈት ዝውውር እንዲያደርጉ ተፈቀደላቸው።
በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒየንስ ሊግና በኮንፌዴሬሽን ካፕ የሚሳተፉት ፋሲል ከነማና ኢትዮዽያ ቡና የዝውውር መስኮቱ ሃምሌ 1/2013 ከመከፈቱ በፊት ዝውውር እንዲያደርጉና ለውድድሩ እንዲዘጋጁ ከተፈቀደላቸው ቀናቶች ተቆጥረዋል።
በዝውውር መስኮቱ ሁለቱም ክለቦች ከተለያዩ ተጨዋቾች ጋር ስማቸው እየተነሳና ለማስፈረም እየጣሩ ሲሆን 200 ሺህ ብር የወር ደመወዝ እየጠየቁ ያሉ ተጨዋቾች መኖራቸው ገበያውን የማይገመት አድርጎታል።
ያም ሆኖ የተጨዋቾች ውል ማብቂያ ሰኔ 30/2013 ድረስ የተጠናቀቀ ዝውውር ላይኖር ይችላል። በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ4 ተጨዋቾችን ውል ያራዘመው ሻምፒዮኑ ንግድ ባንክ የ8 ተጨዋቾች አዲስ ፊርማን ይፋ ለማድረግ ሃምሌ 1/2013 ድረስ እየጠበቀ መሆኑ ተሰምቷል።