በ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ደምቆ በመውጣት የሊጉን ከፍተኛ ግብ አግቢነት ሪከርድ በ ሀያ ዘጠኝ ጎሎች የሰበረው አቡበከር ናስር ከ ጆርጅያ ፈላጊ ክለብ ብቅ ብሏል ።
በ ጆርጅያ የመጀመሪያ ዲቪዝዮን እየተሳተፈ የሚገኘው ዲላ ጎሪ እግር ኳስ ክለብ ይፋዊ የመጀመሪያ ጥያቄያቸውን ለ ኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ አስገብተዋል ።
ዲላ ጎሪ እግር ኳስ ክለብ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ ጆርጅያ ሊግ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል ።
ዲላ ጎሪ ክለብ ከዚህ ቀደም ከ አምስት ዓመት በፊት የ ኤሬቮኑሊ ሊግን ማሸነፍ ሲችሉ በ እ.ኤ.አ 2012 የ ጆርጅያ ዋንጫን ማሸነፍ ችለዋል ።