በአሰልጣኝ ደግአረግ ይግዛዉ እየተመራ የአምናውን ብቃቱን በዚህኛዉ የወድድር አመትም መድገም ያልቻለዉ እና በመጀመሪያዉ ዙር የሊጉ ጉዞም በ22 ነጥቦች 7ተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ የቻለዉ ባህርዳር የቀድሞዉን የፋሲል ከነማ እና ሀዋሳ ከተማ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ሙጂብ ቃሲም ማስፈረሙ ታውቋል።
ከዚህ ቀደም በአፄዎቹ ቤት ቆይታ የነበረዉ እንዲሁም ወደ አልጀሪያ ሊግ አምርቶ ያልተሳካ የስድስት ወራት ቆይታ የነበረዉ አጥቂዉ ሙጅብ ከክለቡ ሀዋሳ ከተማ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ላለፉት ሳምንታት ከጨዋታ ርቆ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን ከክለቡ ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ የጣና ሞገዶቹን መቀላቀሉ ተረጋግጧል።