ለቀጣዩ የውድድር አመት ተሻሽለዉ ለመቅረብ ይረዳቸዉ ዘንድ በቀጣይ ቀናት ወደ ዝውውሩ እንደሚገቡ የሚጠበቁት መድኖች የሁለት ነባር ተጫዋቾቻቸዉን ዉል ለተጨማሪ አመት አድሰዋል።
የእግርኳስ ሂዎቱን በመቱ ከተማ የጀመረዉ እና በከፍተኛ ሊጉ ተሳታፊ ክለብ ኮምቦልቻ ከተማ ፤ ጅማ አባጅፋር እና ባህርዳር ከተማ ከተጫወተ በኋላ በ2015 የውድድር አመት መባቻ ኢትዮጵያ መድንን ተቀላቅሎ ያለፉትን ሁለት አመታት ከክለቡ ጋር ቆይታ ማድረግ የቻለዉ የግብ ዘቡ አቡበከር ኑራ ለተጨማሪ አንድ አመት በክለቡ ለመቆየት ውሉን አራዝሟል።
በተጨማሪም በአሰልጣኝ ገ/መድህን ሀይሌ የሚሰለጥነዉ ኢትዮጵያ መድን ከክለቡ ታዳጊ ቡድን ወደ ዋናዉ ቡድን ባለፈዉ አመት ማደግ ችሎ የነበረዉን መስፍን ዋሼ ለተጨማሪ አንድ አመት ለማቆየት ከስምምነት ላይ ደርሷል።