ከቀናት በፊት በደቡብ አፍሪካዉ ፕሪምየር ሺፕ ተሳታፊ በሆነዉ ፖሎኩዋኔ ሲቲ የሙከራ ዕድል ተመቻችቶለት ወደ ስፍራዉ አቅንቶ የነበረዉ መስፍን ታፈሰ ስኬታማ የሙከራ ጊዜን ማሳለፍ ቢችልም ነገር ግን ከክለቡ ጋር በአንድ አንድ ጉዳዮች ዙሪያ ከስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻሉ ምክንያት ከቀናት በፊት ወደ ሀገር ቤት መመለሱ ይታወሳል።
በኢትዮጵያ ቡና ቤት ያለዉ ውል የተጠናቀቀዉ ተጫዋቹ የቀጣይ ቆይታዉን በተመለከተ እስከአሁን ማረጋገጫ የተገኘ ባይሆንም ነገር ግን የፊት መስመር ተጫዋቹ ከበርካታ የሊጉ ክለቦች የእናስፈርምህ ጥያቄ እየቀረበለት ቢገኝም ነገር ግን ተጫዋቹ ከሌሎቹ ክለቦች በተሻለ ወደ ሲዳማ ቡና ለማምራት ከክለቡ ጋር ንግግር ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።