ወንድሜነህ ደረጀ የባሕር ዳር ከነማ የመጀመርያ ፈራሚ በመሆን ክለቡን ተቀላቅሏል ።
ስም :- ወንድሜነህ ደረጀ
የነበረበት ክለብ:- ኢትዮጵያ ቡና
የተጫወተባቸው ጨዋታዎች : 17 ጨዋታ (1395 ደቂቃ)
ባሕር ዳር ከነማን ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊግ እንዲያድግ ያደረገው ታሪካዊ ስብስብ አባል ነበረ በወቅቱ በጣም ተወዳጅ የነበረው የመሐል ተከላካይ ወንድሜነህ ።
በባሕር ዳር ከነማ በነበረበት ወቅት በነበረው ድንቅ ብቃት በአሰልኞቹ እና ደጋፊዎች ምላጭ እየተባለ ይጠራ የነበረው እና በሰማያዊው ማልያ እጅግ ተወዳጁ ተጫዋች ወንድሜነህ ደረጀ ዳግም ወደ ባሕር ዳር ከነማ ተመልሷል።
በኢትዮጵያ ቡና ቤት ያለፉትን አምስት ዓመታት ያሳለፈው ወንድሜነህ ደረጀ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት እጅግ ድንቅ የተባለ ብቃትን በኢትዮጵያ ቡና ማሳለፍ ችሏል ።
- ማሰታውቂያ -
ሁለተኛው ተጫዋቾች ደግሞ ግርማ ዲሳሳ ወደ ትውልድ ከተማው ክለብ የሚመልሰውን ዝውውር ፈፅሟል ።
ስም : ግርማ ዲሳሳ
የነበረበት ክለብ : መቻል
የሚጫወትበት ቦታ : የመስመር ተከላካይ / የመስመር አጥቂ
የተጫወተው ጨዋታ : 14 ጨዋታ (1234 ደቂቃ)
7 ቁጥር ለባሾች አንዱ የነበረው እና የምንጊዜም የባሕር ዳር ከነማ ታሪካዊ ስብስብ አባል የነበረው ግርማ ዲሳሳ ወደ ባህር ዳር ከነማ ተመልሷል ።
አምስት ዓመታት ከአማራ ፓሊስ ወደ ባህር ዳር ከነማ በመዛወር በቡድኑ ያሳለፈው ተጫዋቹ ከሁለት ዓመት በፊት ክለቡን በመልቀቅ ወደ መቻል ዝውውሩን አከናውኖ ነበር ።
በባሕር ዳር ታዳጊወች ዘንድ በጣም የማወደደው ተጫዋቹ ወደ ፕሪምየር ሊግ ደረጃ ከፍ ወዳለበት ወደ ከተማው ክለብ ዳግም ተመልሷል ።