አርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋችና በ2016 ዓ/ም በፕሪሚየር ሊጉ በፋስል ቤት ድንቅ ቆይታ ያሳለፈውን ይሁን እንዳሻውን አስፈርሟል
ከዚህ ቀደም ከጅማ አባጅፋር ጋር በመሆን 2010 ላይ ፕሪሚየር ሊጉን ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በመተሃራ ፣ ድሬዳዋ ፣ ጂማ ፣ በሀዲያ ሆሳዕና እና ያለፉትን አመታት በፋሲል ቤት ድንቅ አመት ማሳለፍ የቻለው ባለብዙ ልምድ የተከላካይ አማካይ ይሁን እንዳሻው ለአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የፈረመ ቀዳሚው አዲስ ተጫዋቾች ሆኗል።