አርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ሁለተኛውን አዲስ የክለቡን ፈራሚ የውድድር ዘመኑን በከፍተኛ ሊጉ በደሴ ከተማ ጥሩ የውድድር ዘመን ያሳለፈውን አጥቂ ሙልጌታ ካሳሁንን ሁለተኛ አዲስ ፈራሚ አድርጎ አስፈርሟል።
አርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በፕሪሚየር ሊጉም ጥንካሬውን ለማስቀጠል የክለቡ ነባር ተጨዋቾችን ውል የማደስና አዳዲስ ተጨዋቾችን ወደክለቡ የማቀላቀል ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል።
አርባምንጭ ከተማ ከዚህ ቀደም በቤንችማጂ ቡራዩ ከነማና በ2016 ዓ/ም በከፍተኛ ሊጉ በደሴ ከተማ ድንቅ የውድድር ዓመት ማሳለፍ የቻለውን ሙልጌታ ካሳሁንን አስፈርሟል።