አዳማ ከነማ ሁለት ጋናዊያን ተጫዋቾችን አስፈርሟል !!
አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለን በዋና አሰልጣኝነት ከሾሙ በኋላ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር ገበያ ላይ በርከት ያሉ አዳዲስ ተጫዋችን ማስፈረም የቻሉት አዳማ ከተማዎች ተጨማሪ ሁለት የጋና ዜግነት ያላቸዉን ተጫዋቾች ማስፈረማቸዉ ተረጋግጧል።
ከዚህ ቀደም ለጋናዉ አሳንቴ ኮቶኮ መጫወት የቻለዉ ግብ ጠባቂዉ ክዋሜ ባህ እና የዉድድር አመቱን በኸርትስ ኦፍ አታኪንግ ማሳለፍ የቻለዉ የአጥቂ አማካዩ ፍሬድሪክ አንሳህ ቦችዋይ አንድ አመት በሚቆይ የስምምነት ዉል አዳማ ከተማን መቀላቀላቸው ተረጋግጧል።