የዝውውር መስኮቱ ከተከፈተ አንስቶ ለቀናንት ያህል የነባር ተጫዋቾቻቸውን እና አሰልጣኛቸዉን ዉል በማደስ ላይ የነበሩት የጦና ንቦቹ በዛሬዉ ዕለት ሁለተኛ ፈራሚ በማድረግ አማካዩን በሀይሉ ተሻገርን ወደ ስብስባቸዉ መቀላቀል ችለዋል።
ከዚህ ቀደም ለኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ለወልቂጤ ከተማ መጫወት የቻለዉ አማካዩ አንድ አመት በሚቆይ የስምምነት ዉል ለወላይታ ድቻ ለመጫወት ፊርማዉን ማኖሩ ተረጋግጧል።